የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘አፈጣጠራችን ድንቅ’ ነው
    መጠበቂያ ግንብ—2007 | ሰኔ 15
    • አስደናቂ የሆነው አእምሯችን

      12. ሰዎችን ከእንስሳት ልዩ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው?

      12 “አቤቱ፣ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው! ቊጥራቸውም እንደ ምን በዛ! ብቈጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ።” (መዝሙር 139:17, 18ሀ የ1954 ትርጉም) እንስሳትም ቢሆኑ ድንቅ ሆነው ተፈጥረዋል። እንዲያውም የተወሰኑ እንስሳት በአንዳንድ መንገዶች ከሰዎች የላቁ ችሎታዎች አሏቸው። ሆኖም አምላክ ለሰዎች ከማንኛውም እንስሳ በእጅጉ የሚልቅ የማሰብ ችሎታ ሰጥቷቸዋል። አንድ የሳይንስ መጽሐፍ “እኛ ሰዎች ከሌሎች እንስሳት ጋር በብዙ መንገዶች የምንመሳሰል ብንሆንም በቋንቋና በማሰብ ችሎታችን በምድር ካሉ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ የተለየን ነን። በተጨማሪም ስለ ራሳችን ለማወቅ ባለን ከፍተኛ ጉጉት ከሌሎች እንለያለን። አካላችን የተገነባው እንዴት ነው? እንዴት ተሠራን? እንደሚሉት ያሉ ጥያቄዎችን እንጠይቃለን።” ዳዊትም በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ ያሰላስል ነበር።

      13. (ሀ) ዳዊት በአምላክ ሐሳቦች ላይ ለማሰላሰል የቻለው እንዴት ነው? (ለ) እኛስ የዳዊትን ምሳሌ እንዴት መኮረጅ እንችላለን?

      13 ከሁሉም በላይ ከእንስሳት የተለየን የሚያደርገን በአምላክ ሐሳቦች ላይ ማሰላሰል መቻላችን ነው።c ይህ ልዩ ስጦታ ‘በአምላክ መልክ’ መፈጠራችን የሚታይበት አንዱ መንገድ ነው። (ዘፍጥረት 1:27) ዳዊት ይህንን ስጦታ በሚገባ ተጠቅሞበታል። ዳዊት የአምላክን መኖር በሚያሳዩት ማስረጃዎችና በዙሪያው ባሉት ነገሮች ላይ በሚንጸባረቁት የአምላክ ግሩም ባሕርያት ላይ ያሰላስል ነበር። በተጨማሪም ዳዊት፣ አምላክ ስለ ራሱና ስለ ሥራዎቹ የተናገራቸውን ሐሳቦች የያዙት የቅዱሳን መጻሕፍት የመጀመሪያዎቹ ክፍሎች ነበሩት። በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉት እነዚህ መጻሕፍት የአምላክን ሐሳቦች፣ ባሕርያትና ዓላማ እንዲረዳ አስችለውታል። ዳዊት በቅዱሳን መጻሕፍት፣ በፍጥረት ሥራዎችና ከአምላክ ጋር ባለው ግንኙነት ላይ ማሰላሰሉ ፈጣሪውን እንዲያወድስ ገፋፍቶታል።

  • ‘አፈጣጠራችን ድንቅ’ ነው
    መጠበቂያ ግንብ—2007 | ሰኔ 15
    • c ዳዊት በመዝሙር 139:18ለ ላይ የተናገራቸው ቃላት ከጠዋት ጀምሮ ማታ እስኪተኛ ድረስ የይሖዋን ሐሳቦች ቢቆጥር፣ በማግስቱ ጠዋት ሲነቃም የሚቆጥረው እንደማያጣ የሚያሳዩ ይመስላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ