የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋ ታላቅነት የማይመረመር ነው
    መጠበቂያ ግንብ—2004 | ጥር 15
    • የይሖዋ ባሕርያት ታላቅነቱን ያጎላሉ

      20, 21. (ሀ) መዝሙር 145:7-9 የይሖዋን ታላቅነት የሚያጎላው ከየትኞቹ ባሕርያቱ አንጻር ነው? (ለ) እነዚህ የአምላክ ባሕርያት እርሱን ለሚወዱት ሁሉ ምን ጥቅም ያስገኙላቸዋል?

      20 እስከ አሁን እንደተመለከትነው የመዝሙር 145 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ቁጥሮች ወደር የለሽ በሆነው ታላቅነቱ ላከናወናቸው ነገሮች ይሖዋን የምናወድስበትን አሳማኝ ምክንያት ይዘዋል። ከ7 እስከ 9 ያሉት ቁጥሮች ደግሞ የይሖዋን ባሕርያት በመጥቀስ ታላቅነቱን ያጎላሉ። ዳዊት እንዲህ በማለት ዘምሯል:- “የቸርነትህን [“የጥሩነትህን፣” NW] ብዛት መታሰብ ያወጣሉ፣ በጽድቅህም ሐሤትን ያደርጋሉ። እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፣ ከቁጣ የራቀ፣ ምሕረቱም ብዙ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር [“ለሁሉም ጥሩ፣” NW] ነው። ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው።”

      21 እዚህ ላይ ዳዊት በመጀመሪያ የጠቀሰው ሰይጣን ዲያብሎስ ጥያቄ ያስነሳባቸውን የይሖዋ ባሕርያት ይኸውም ጥሩነቱንና ጽድቁን ነው። ይሖዋ እነዚህ ባሕርያት ያሉት መሆኑ እርሱን ለሚወዱትና ለመንግሥቱ ለሚገዙት ምን ጥቅም ያስገኝላቸዋል? የይሖዋ ጥሩነትና የጽድቅ አገዛዙ ለአምላኪዎቹ ከፍተኛ ደስታ ስለሚያመጣላቸው እርሱን ያለማቋረጥ ያወድሳሉ። ከዚህም በላይ ይሖዋ ጥሩነቱን የሚያሳየው “ለሁሉም” ነው። ይህም ሌሎች በርካታ ሰዎች ጊዜው ከማለፉ በፊት ንስሐ ገብተው እውነተኛውን አምላክ ለማምለክ አጋጣሚ እንደሚሰጣቸው ተስፋ እናደርጋለን።—የሐዋርያት ሥራ 14:15-17

      22. ይሖዋ አገልጋዮቹን የሚይዘው እንዴት ነው?

      22 ዳዊት፣ ይሖዋ በሙሴ ፊት ባለፈ ጊዜ “እግዚአብሔር፣ እግዚአብሔር መሐሪ፣ ሞገስ ያለው፣ ታጋሽም፣ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት” በማለት ለጠቀሳቸው ባሕርያቱም አድናቆት ነበረው። (ዘጸአት 34:6) በመሆኑም “እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፣ ከቁጣ የራቀ፣ ምሕረቱም [“ፍቅራዊ ደግነቱ፣” NW] ብዙ ነው” ለማለት ችሏል። ይሖዋ ታላቅነቱ ይህ ነው የማይባል ቢሆንም ሰብዓዊ አገልጋዮቹን በርኅራኄ በመያዝ ያከብራቸዋል። እንዲሁም መሐሪ ስለሆነ ንስሐ የሚገቡ ኃጢአተኞችን በኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት ይቅር ለማለት ፈቃደኛ ነው። በተጨማሪም ይሖዋ ከቁጣ የራቀ ወይም ታጋሽ በመሆኑ አገልጋዮቹን ጽድቅ በሰፈነበት አዲስ ዓለም ከመግባት ሊያግዷቸው የሚችሉ ድክመቶቻቸውን እንዲያስወግዱ አጋጣሚ ይሰጣቸዋል።—2 ጴጥሮስ 3:9, 13, 14

  • ይሖዋ ፍቅራዊ ደግነቱ ብዙ ነው
    መጠበቂያ ግንብ—2004 | ጥር 15
    • ይሖዋ ፍቅራዊ ደግነቱ ብዙ ነው

      “ይሖዋ . . . ፍቅራዊ ደግነቱ ብዙ ነው።”—መዝሙር 145:8 NW

      1. አምላክ ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር ምን ያህል ነው?

      “እግዚአብሔር ፍቅር ነው።” (1 ዮሐንስ 4:8) ይህ ልብን ደስ የሚያሰኝ አባባል የይሖዋ አገዛዝ በፍቅር ላይ የተመሠረተ መሆኑን ያሳያል። ለእርሱ የማይታዘዙ ሰዎች እንኳን በፍቅር ተነሳስቶ ከሰጠን ዝናብና ፀሐይ ተጠቃሚ መሆናቸው ይህን ያረጋግጣል። (ማቴዎስ 5:44, 45) ይሖዋ መላውን የሰው ዘር ስለሚወድድ ጠላቶቹ እንኳን ንስሐ ገብተው ወደ እርሱ ሊመለሱና የዘላለም ሕይወት ሊያገኙ ይችላሉ። (ዮሐንስ 3:16) ይሁን እንጂ እርሱን የሚወድዱ ሰዎች ጽድቅ በሰፈነበት አዲስ ምድር ውስጥ የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ ከስህተታቸው የማይታረሙትን ክፉ ሰዎች በቅርቡ ጠራርጎ ያጠፋቸዋል።—መዝሙር 37:9-11, 29፤ 2 ጴጥሮስ 3:13

      2. ይሖዋ ራሳቸውን ለወሰኑ አገልጋዮቹ ምን ዓይነት ፍቅር ያሳያል?

      2 ይሖዋ ለእውነተኛ አምላኪዎቹ ያለው ፍቅር ጥልቅ እና ዘላለማዊ ነው። ይህ ፍቅር “ፍቅራዊ ደግነት” ወይም “ዘላለማዊ ፍቅር” ተብለው በተተረጎሙት የዕብራይስጥ ቃላት ተገልጿል። የጥንቷ እስራኤል ንጉሥ የነበረው ዳዊት ለይሖዋ ፍቅራዊ ደግነት ከፍተኛ አድናቆት ነበረው። ከግል ተሞክሮው በመነሳት እንዲሁም አምላክ ከሌሎች ጋር በነበረው ግንኙነት ላይ በማሰላሰል “ይሖዋ . . . ፍቅራዊ ደግነቱ [ወይም “ዘላለማዊ ፍቅሩ”] ብዙ ነው” በማለት በሙሉ ልብ መዘመር ችሏል።—መዝሙር 145:8 NW

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ