የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሲኦል ምን ዓይነት ቦታ ነው?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
    • 6. (ሀ) ሺኦልና ሐዴስ አንድ መሆናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሳየው እንዴት ነው? (ለ) ኢየሱስ በሐዴስ ውስጥ የነበረ መሆኑ ምን ያሳያል?

      6 ይህንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ሺኦል የሚለው የዕብራይስጥ ቃልና ሐዴስ የሚለው የግሪክኛ ቃል አንድ መሆናቸውን ግልጽ እናድርግ። በእንግሊዝኛው የአሜሪካን ስታንዳርድ ቨርሽን ላይ በዕብራይስጥ ጽሑፎች ውስጥ የሚገኘውን መዝሙር 16:10⁠ንና በክርስቲያን ግሪክኛ ጽሑፎች ውስጥ የሚገኘውን ሥራ 2:31⁠ን ማስተያየት ይህንን ግልጽ ያደርገዋል። እነዚህንም ጥቅሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ልትመለከታቸው ትችላለህ። ሺኦል ከሚገኝበት ከመዝሙር 16:10 ላይ በመጥቀስ ሥራ 2:31 ሐዴስ በሚለው ቃል ይጠቀማል። ኢየሱስ ክርስቶስ በሐዴስ ወይም በሲኦል እንደነበረ አስተውል። አምላክ ኢየሱስን በእሳታማ ሲኦል ውስጥ አሰቃይቶታል ብለን ልናምን ነውን? በፍጹም ሊሆን አይችልም! በቀላል አነጋገር ኢየሱስ በመቃብር ውስጥ ነበር ማለት ነው።

  • ሲኦል ምን ዓይነት ቦታ ነው?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
    • [በገጽ 83 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

      “ሺኦል” የሚለው የዕብራይስጥ ቃልና “ሐዴስ” የሚለው የግሪክኛ ቃል ትርጉማቸው አንድ ነው።

      መዝሙር 16:10

      ፱ ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፤ ምላሴም ሐሴት አደረገች፤ ሥጋዬ ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤ ፲ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም። የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ደስታን አጠገብኸኝ፤ በቀኝህም የዘለላለም

      በዕብራይስጡ ላይ “ሺኦል” ይላል

      ሥራ 2:31

      ፴፩ ከወገቡም ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደ ማለለት ስለ አወቀ፤ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ። ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ