-
ፍጥረት የአምላክን ክብር ያውጃል!መጠበቂያ ግንብ—2004 | ሰኔ 1
-
-
7 ይሁን እንጂ ይህን ምሥክርነት ለመስማት አስተዋይ መሆን ያስፈልጋል። “ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤ ድምፃቸው በጆሮ የሚሰማ አይደለም።” ሆኖም ሰማያት ያለ ድምፅ የሚሰጡት ምሥክርነት በጣም አሳማኝ ነው። “ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፤ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ይወጣል።” (መዝሙር 19:3, 4) ሰማያት ምሥክርነታቸው ከምድር ጫፍ እስከ ምድር ጫፍ እንዲሰማ ድምፃቸውን አስተጋብተዋል ሊባል ይችላል።
8, 9. ፀሐይን በተመለከተ ያሉት አንዳንድ አስደናቂ ሐሳቦች ምንድን ናቸው?
8 ከዚህ በመቀጠል ዳዊት ይሖዋ ስለፈጠረው ሌላ አስደናቂ ነገር ገልጿል:- “እርሱ በሰማያት ለፀሓይ ድንኳን ተክሎአል፤ ፀሓይም ከእልፍኙ እንደሚወጣ ሙሽራ ይወጣል፤ ወደ ግቡም እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል። መውጫው ከሰማያት ዳርቻ ነው፤ ዑደቱም እስከ ሌላኛው ዳርቻ ነው፤ ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።”—መዝሙር 19:4-6
-
-
ፍጥረት የአምላክን ክብር ያውጃል!መጠበቂያ ግንብ—2004 | ሰኔ 1
-
-
10. (ሀ) ፀሐይ ወደ ‘ድንኳንዋ’ የምትገባውና ከዚያ የምትወጣው እንዴት ነው? (ለ) ፀሐይ እንደ “ብርቱ ሰው” የምትሮጠው እንዴት ነው?
10 መዝሙራዊው ፀሐይን በቀን ከአንዱ አድማስ ወደ ሌላው እንደሚሮጥና ሲመሽ ደግሞ ‘ድንኳኑ’ ውስጥ እንደሚገባ “ብርቱ ሰው” አድርጎ ይገልጻታል። ይህች ግዙፍ ኮከብ ከአድማስ ባሻገር ስትጠልቅ፣ ምድር ሆኖ ለሚያያት ሰው ለእረፍት ወደ “ድንኳን” የምትገባ፤ ጎህ ሲቀድ ደግሞ “ከእልፍኙ እንደሚወጣ ሙሽራ” በድንገት ቦግ ብላ የምትወጣ ትመስላለች። ዳዊት እረኛ ስለነበር ማታ ማታ በጣም እንደሚቀዘቅዝ ያውቃል። (ዘፍጥረት 31:40) የፀሐይ ጨረር እርሱንም ሆነ አካባቢውን ወዲያውኑ እንደሚያሞቅም ትዝ ይለዋል። በግልጽ ማየት እንደሚቻለው ፀሐይ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ የምታደርገው “ጉዞ” ታክቷት አያውቅም፤ እንዲያውም እንደ “ብርቱ ሰው” ጉዞውን ለመድገም ምንጊዜም ዝግጁ ነች።
-