የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋን ክንዶች መደገፊያህ ማድረግ
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | ጥቅምት 1
    • 15. በመዝሙር 19:7-13 ላይ የሚገኙት የዳዊት ቃላት የያዙት ቁም ነገር ምንድን ነው?

      15 የይሖዋን ሕግ የምናፈቅር ብንሆንም እንኳ አልፎ አልፎ እንሳሳታለን። ይህ ጭንቀት እንደሚፈጥርብን አያጠራጥርም። የአምላክን ሕጎች፣ ማሳሰቢያዎች፣ ትዕዛዞችና የፍርድ ውሳኔዎች ከወርቅ የበለጠ ይወድ የነበረው ዳዊትም ቢሆን ይህ ነገር ደርሶበታል። እርሱ እንዲህ አለ፦ “ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል። ስህተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ። የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፣ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።” (መዝሙር 19:7-13) እስቲ እነዚህን ቃላት እንመርምር።

  • የይሖዋን ክንዶች መደገፊያህ ማድረግ
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | ጥቅምት 1
    • 17. የተደበቁ ኃጢአቶች አንድን ሰው የሚጎዱት እንዴት ነው? ሆኖም ይቅርታና እፎይታ ሊገኝ የሚችለው እንዴት ነው?

      17 የተደበቁ ኃጢአቶች ጭንቀትን ሊፈጥሩ ይችላሉ። በመዝሙር 32:1-5 ላይ እንደተገለጸው ዳዊት ኃጢአቱን ለመደበቅ ሞክሮ ነበር፣ ሆኖም እንዲህ አለ፦ “ዝም ባልሁ ጊዜ አጥንቶቼ ተበላሹ፤ በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና፣ እርጥበቴም ለበጋ ትኩሳት ተለወጠ።” ይወቅሰው የነበረውን ኅሊና ዝም ለማሰኘት መሞከሩ ዳዊትን አድቅቆት ነበር፤ ዳዊት በጭንቀቱ ምክንያት በድርቅ ወይም በበጋ ሐሩር እርጥበቱን አጥቶ እንደደረቀ ዛፍ ኃይል አጥቶና ጠውልጎ ነበር። በአእምሮውም ሆነ በአካሉ ጉዳት አስከትሎበት እንደነበር ግልጽ ነው፤ ኃጢአቱን ሳይናዘዝ በመቅረቱም ደስታውን አጥቶ ነበር። ይቅርታንና እፎይታን ሊያገኝ የሚችለው ለአምላክ ኃጢአቱን ቢናዘዝ ብቻ ነው። ዳዊት እንዲህ አለ፦ “መተላለፉ የቀረችለት ኃጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው። . . . ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፣ በደሌንም አልሸፈንሁም፤ [ለይሖዋ (አዓት)] መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ።” ከክርስቲያን ሽማግሌዎች የሚገኝ ፍቅራዊ እርዳታ መንፈሳዊ ፈውስ ለማግኘት ሊረዳ ይችላል።​—ምሳሌ 28:13፤ ያዕቆብ 5:13-20

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ