-
የአምላክ ወዳጅ መሆን የምችለው እንዴት ነው?ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 2
-
-
ከአምላክ ጋር ባለህ ወዳጅነት ረገድ ልትዘነጋው የማይገባ ሌላም ነገር አለ። መዝሙራዊው ዳዊት “እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ” በማለት ጽፏል። (መዝሙር 34:8) ዳዊት 34ኛውን መዝሙር ከማቀናበሩ ትንሽ ቀደም ብሎ በጣም አስፈሪ ሁኔታ አጋጥሞት ነበር። በወቅቱ ሊገድለው ከሚፈልገው ከንጉሥ ሳኦል እየሸሸ ነበር፤ ይህ በራሱ በጣም አስጨናቂ ነገር ሆኖ ሳለ ዳዊት ጠላቶቹ ወደሆኑት ፍልስጥኤማውያን በመሄድ መሸሸግ ግድ ሆኖበት ነበር። ዳዊት ከሞት ጋር በተፋጠጠበት በዚያ ወቅት እንዳበደ ሰው በመሆን በዘዴ ማምለጥ ችሏል።—1 ሳሙኤል 21:10-15
ዳዊት ከሞት ለጥቂት ሊያመልጥ የቻለው በራሱ ብልሃት እንደሆነ አልተሰማውም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እንደረዳው ገልጿል። ከላይ በተጠቀሰው መዝሙር ላይ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ እርሱም መለሰልኝ፤ ከፍርሀቴም ሁሉ አዳነኝ።” (መዝሙር 34:4) ከዚህ ለማየት እንደምንችለው ዳዊት “እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ” ብሎ ሌሎችን የመከረው ከራሱ ተሞክሮ በመነሳት ነበር።a
-
-
የአምላክ ወዳጅ መሆን የምችለው እንዴት ነው?ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 2
-
-
a አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች “ቀምሳችሁ እዩ” የሚለውን ሐረግ “ራሳችሁ ተመልከቱ፣” “ራሳችሁ ድረሱበት” እንዲሁም “ከተሞክሮ ታያላችሁ” በማለት አስቀምጠውታል።—ኮንቴምፖራሪ ኢንግሊሽ ቨርዥን፣ ቱዴይስ ኢንግሊሽ ቨርዥን እና ዘ ባይብል ኢን ቤዚክ ኢንግሊሽ
-