-
በስጦታ ላገኘነው ሕይወት አድናቆት ይኑርህለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
2. የይሖዋ ስጦታ ለሆነው ሕይወት አድናቆት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ይሖዋ ለአንተ ያለውን ፍቅርና አሳቢነት ማሳየት የጀመረው በእናትህ ማህፀን ውስጥ ከተፀነስክበት ጊዜ አንስቶ ነው። የአምላክ አገልጋይ የነበረው ዳዊት “ፅንስ እያለሁ እንኳ ዓይኖችህ አዩኝ” በማለት በመንፈስ መሪነት ተናግሯል። (መዝሙር 139:16) የአንተ ሕይወት በይሖዋ ፊት በጣም ውድ ነው። (ማቴዎስ 10:29-31ን አንብብ።) የሌላን ሰው ሌላው ቀርቶ የራስን ሕይወት ሆን ብሎ ማጥፋት አምላክን በጣም ያሳዝነዋል።a (ዘፀአት 20:13) ሳያስፈልግ ሕይወታችንን አደጋ ላይ መጣላችን ወይም የሌሎችን ሕይወት ከአደጋ ለመጠበቅ ተገቢውን ጥንቃቄ አለማድረጋችንም አምላክን ያሳዝነዋል። የራሳችንን ሕይወት ከአደጋ በመጠበቅና ለሌሎች ሕይወት አክብሮት በማሳየት ግሩም ለሆነው የሕይወት ስጦታ አድናቆት እንዳለን እናሳያለን።
-
-
በስጦታ ላገኘነው ሕይወት አድናቆት ይኑርህለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
a ይሖዋ ልባቸው ለተሰበረ ሰዎች ከልብ ያስባል። (መዝሙር 34:18) አንድ ሰው ራሱን ለማጥፋት የሚገፋፋውን የስሜት ሥቃይ የሚረዳ ከመሆኑም ሌላ እንዲህ የሚሰማውን ሰው መርዳት ይፈልጋል። አምላክ የሚሰጠው እርዳታ ራሳቸውን ለማጥፋት የሚያስቡ ሰዎችን ምን ያህል እንደሚጠቅም ለማየት በዚህ ምዕራፍ ውስጥ “ምርምር አድርግ” በሚለው ክፍል ሥር የተጠቀሰውን “ራሴን የማጥፋት ሐሳብ ሲመጣብኝ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳኝ ይችላል?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።
-