-
“የሰላሙ መስፍን” በጠላቶቹ መካከል ሲገዛ“የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
-
-
4–6. (ሀ) ኢየሱስ “የሰላም መስፍን” በመሆን መግዛት ከመጀመሩ በፊት ዓለም በሙሉ ወደ ክርስትና እስኪለወጥ ድረስ መጠበቅ እንደሌለበት መዝሙር ምዕራፍ 2 የሚያመለክተው እንዴት ነው? (ለ) መዝሙር 2:7 በየትኛው ጊዜ ላይ ተፈጽሟል?
4 ስለዚህ በግልጽ እንደሚታየው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ዳዊት ልጅ በመሆን መግዛት የሚጀምረው ዓለም በመላው ወደ ክርስትና ከተለወጠ በኋላ አይደለም። ከዚያ ይልቅ መግዛት የሚጀምረው በመጨረሻ ላይ ይሖዋ አምላክ በውጊያ ላነገሠው ልጁ የእግር መርገጫ እንዲሆኑ በሚያደርግለት በጠላቶቹ መካከል ነው። መዝሙር ምዕራፍ 2ም እንደዚሁ “የሰላም መስፍን” በመሆን በጠላቶቹ መካከል መግዛት እንደሚጀምር በሚከተሉት ቃላት ያመለክታል:-
5 “አሕዛብ ለምን ያጉረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ? የምድር ነገሥታት ተነሱ፣ አለቆችም (በይሖዋና አዓት) (በመሲሑ አዓት) ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ:- ‘ማሰሪያቸውን እንበጥስ፣ ገመዳቸውን ከእኛ እንጣል።’ በሰማይ የሚኖር እርሱ ይስቃል፣ (ይሖዋ አዓት) ይሳለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜም በቁጣው ይናገራቸዋል፣ በመዓቱም ያውካቸዋል። [እንዲህ በማለት] ‘እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጸዮን ላይ።”
-
-
“የሰላሙ መስፍን” በጠላቶቹ መካከል ሲገዛ“የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
-
-
7. ከጴንጠቆስጤ ቀን በኋላ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት መዝሙር 2ን በመጥቀስ ምን አሉ?
7 በሥራ 4:24-27 መሠረት በ33 እዘአ ከዋለው የጴንጠቆስጤ ዕለት በኋላ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት በመዝሙር ምዕራፍ ሁለት ላይ ያለውን እንደሚከተለው ጠቅሰው ነበር:- “በአንድ ልብ ሆነው ድምፃቸውን ወደ እግዚአብሔር ከፍ አደረጉ እንዲህም አሉ:- ‘ጌታ ሆይ፣ አንተ ሰማይና ምድሩን ባሕሩንም በእነርሱም የሚኖረውን ሁሉ የፈጠርህ በመንፈስ ቅዱስም በብላቴናህ (በአገልጋይህ) በአባታቸን በዳዊት አፍ አሕዛብ ለምን አጉረመረሙ? ሕዝቡስ ከንቱን ነገር ለምን አሰቡ? የምድር ነገሥታት ተነሱ አለቆችም (በይሖዋና) በተቀባው ላይ አብረው ተከማቹ ብለህ የተናገርህ አምላክ ነህ። በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።”
የመዝሙር ምዕራፍ 2 ዋነኛ ፍፃሜ
8. (ሀ) መዝሙር 2:1,2 የመጀመሪያ ተፈጻሚነቱን ያገኘው መቼ ነበር? (ለ) መዝሙር ምዕራፍ 2 ዋነኛ ተፈጻሚነቱን ያገኘው ከመቼ ጀምሮ ነው?
8 በመጀመሪያው መቶ ዘመን 33ኛው ዓመት የመዝሙር 2:1,2ን ትንቢታዊ ቃላት የመጀመሪያ ፍጻሜ ተመልክቶአል። ይህም በምድር ላይ ሰው ከነበረው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ነበር። እርሱም በመጥምቁ ዮሐንስ በተጠመቀበት ጊዜ በይሖዋ አምላክ ቅዱስ መንፈስ ተቀብቶ ነበር። ሆኖም መዝሙር 2 ዋነኛ ፍጻሜውን ያገኘው በ1914 ከተፈጸመው የአሕዛብ ዘመናት ወዲህ ነው። (ሉቃስ 21:24) በ607 ከዘአበ የኢየሩሳሌም ከተማ በመጀመሪያ ከጠፋችበት ጊዜ የሚጀምሩት “የተወሰኑት የአሕዛብ ዘመናት” በ1914 እንደተፈጸሙ በበቂ ሁኔታ ተረጋግጧል።a በዚያን ጊዜ ለዚህ ዓለም ብሔራት፣ ሕዝበ ክርስቲያን ነን ለሚሉት ብሔራት ጭምር የሞት ደወል ተደውሏል።
9. በዳዊት ንጉሣዊ መስመር ከተወከለው የአምላክ መንግሥት ጋር በተያያዘ ሁኔታ በመጀመሪያው የኢየሩሳሌም ጥፋት ወቅት ምን ነገር ተፈጸመ?
9 ኢየሩሳሌም በመጀመሪያ በባቢሎናውያን በጠፋችበት ጊዜ በንጉሥ ዳዊት ንጉሣዊ መስመር የተወከለውና በእስራኤል ሕዝብ ላይ ይገዛ የነበረው የይሖዋ አምላክ መንግሥት ወደ ፍጻሜው መጥቶአል። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ሥጋዊ አይሁዳውያን ከንጉሥ ዳዊት መስመር በሆነ ንጉሥ አልተገዙም። ይሁን እንጂ ባንተ የትውልድ መስመር ዘላለማዊ መንግሥት አቋቍማለሁ በማለት ይሖዋ ቃል ኪዳን ባደረገለት በዳዊት ዘር የሚመራው የልዑሉ አምላክ መንግሥት በምድር ላይ ለዘላለም ተቋርጦ የሚቀር አልነበረም።
10, 11. (ሀ) በነቢዩ ሕዝቅኤል በኩል አምላክ የዳዊትን ዙፋን በሚመለከት ምን አለ? (ለ) የዳዊትን ዙፋን ለመውረስ “ሕጋዊ መብት ያለው” ሆኖ የመጣው ማን ነው? (ሐ) እርሱስ ራሱን እንደ ሕጋዊ ወራሽ አድርጎ ባቀረበ ጊዜ የተሰበሰቡት ብዙ አይሁዳውያን ምን አሉ?
10 ኢየሩሳሌም ለመጀመሪያ ጊዜ ከመጥፋቷ ከጥቂት ጊዜ በፊት ይሖዋ ነቢዩን ሕዝቅኤልን ለንጉሥዋ የሚከተሉትን ቃላት እንዲነግረው አነሳሳው:- “አንተ ቀንህ የደረሰብህ፣ የኃጢአትህ ቀጠሮ ጊዜ የደረሰብህ፣ ርኩስ ኃጢአተኛ የእስራኤል አለቃ ሆይ፣ ጌታ (ይሖዋ አዓት) እንዲህ ይላል:- መጠምጠሚያውን አውልቅ፣ ዘውዱንም አርቅ፤ ይህ እንዲህ አይሆንም፤ የተዋረደውን ከፍ አድርግ፣ ከፍ ያለውንም አዋርድ። ባድማ፣ ባድማ፣ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ‘ፍርድ ያለው (ሕጋዊ መብት ያለው አዓት) እስኪመጣ ድረስ ይህች ደግሞ አትሆንም፣ ለእርሱም እሰጣታለሁ።’”— ሕዝቅኤል 21:25–27
11 ‘ሕጋዊ መብት ያለው’ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆኖ ተገኝቷል። ከዳዊት የትውልድ መስመር የመጣ መሆኑም በማቴዎስ 1:1–16 እና በሉቃስ 3:23–31 ተመዝግቦ ይገኛል። በአብዛኛው “የዳዊት ልጅ” ተብሎ ይጠራ ነበር። ትንቢቱን ለመፈጸም በአህያ ውርንጭላ ላይ እየጋለበ በድል ወደ ኢየሩሳሌም በገባበት ቀን እርሱንና ሐዋርያቱን ተከትለው የሄዱት የአይሁድ ሕዝቦች በደስታ ተውጠው:- “(ማዳን) ለዳዊት ልጅ (በይሖዋ አዓት) ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሣዕና በአርያም” እያሉ ይጮሁ ነበር።— ማቴዎስ 21:9
“የዳዊት ልጅ” በሰማይ በዙፋን ላይ ተቀመጠ
12. የአሕዛብ ዘመናት በ1914 ሲፈጸሙ ኢየሱስ ክርስቶስ የዳዊት ዘላለማዊ ወራሽ በመሆን ዙፋን ላይ የተቀመጠው የት ነበር?
12 በዳዊት ቤተሰብ እጅ የነበረውን የአምላክን መንግሥት አሕዛብ በእግራቸው የረገጡባቸው 2520 ዓመታት በ1914 ተፈጽመዋል። በዚያን ጊዜም “የዳዊት ልጅ” የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ ሆኖ የሚሾምበት ጊዜ መጣ። ይህም የሆነው በምድራዊ ዙፋን ላይ ሳይሆን በጣም ከፍተኛ በሆኑት በሰማያት ውስጥ በይሖዋ አምላክ ቀኝ ነበር!— ዳንኤል 7:9,10,13,14
13. (ሀ) 1914 የአሕዛብ ዘመናት መጨረሻ እንደሚሆን አስቀድሞ ሲገለጽ የነበረው ከየትኛው ጊዜ ጀምሮ ነው? በእነማን አማካኝነትስ? (ለ) የምድር መንግሥታት ዙፋን ላይ ለተቀመጠው አዲስ ንጉሥ ለ“ዳዊት ልጅ” የነበራቸው ዝንባሌ ምን ነበር?
13 ይህ ከፍተኛ የሆነ ቀን ከመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና የትናንሽ ጽሑፎች ማኅበር ጋር የቅርብ ግንኙነት በነበራቸው ሰዎች ከ1876 ጀምሮ አስቀድሞ ተጠቍሞ ነበር። ይሁን አንጂ የምድር መንግሥታት፣ ሕዝበ ክርስቲያን ነን የሚሉ መንግሥታት ጭምር የበላይ ገዥነታቸውን አዲስ ለተሾመው “የዳዊት ልጅ” የሚያስረክቡበት ጊዜ መድረሱን ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑም። የይሖዋ አምላክ የእግር መርገጫ በሆነችው በመላዋ ምድር ላይ ከአምላክ የተሰጠውን የበላይ ገዥነት መብት እንደያዘ አልተቀበሉም። (ማቴዎስ 5:35) ሕጋዊ የሆነውን ንጉሥ በግልጽ አንቀበልም ማለታቸውን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ በመግባት አረጋግጠዋል።
-