-
‘በይሖዋ ደስ ይበላችሁ’መጠበቂያ ግንብ—2003 | ታኅሣሥ 1
-
-
“አትቅና”
3, 4. መዝሙር 37:1 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው ዳዊት ምን ምክር ሰጥቷል? በዛሬው ጊዜ ምክሩን መከተላችን ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው?
3 የምንኖረው ‘አስጨናቂ በሆነ ዘመን’ ውስጥ ከመሆኑም ሌላ ክፋት በእጅጉ ተስፋፍቶ ይገኛል። “ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፣ እያሳቱና እየሳቱ፣ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ” የሚሉት የሐዋርያው ጳውሎስ ቃላት ሲፈጸሙ ተመልክተናል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1, 13) ክፉ ሰዎች የተሳካላቸውና ብልጽግና ያገኙ መስለው መታየታቸው ብቻ እንኳ ተጽዕኖ ሊያሳድርብን ይችላል! ይህ መንፈሳዊ እይታችን እንዲዛባ በማድረግ አቅጣጫችንን ሊያስተን ይችላል። የመዝሙር 37 የመክፈቻ ቃላት “በክፉዎች ላይ አትቅና [“አትበሳጭ፣” የ1980 ትርጉም]፣ ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና” በማለት ይህን ከባድ አደጋ በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ይሰጡናል።
4 የዓለማችን መገናኛ ብዙኃን የፍትሕ መጓደልን በተመለከተ በየዕለቱ በርካታ ዘገባዎች ያቀርባሉ። አጭበርባሪ ነጋዴዎች ከመያዝ ያመልጣሉ። ወንጀለኞች ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሰዎችን መጠቀሚያ ያደርጓቸዋል። ነፍሰ ገዳዮች ሳይያዙ ወይም ሳይቀጡ ይቀራሉ። የፍትሕ መዛባት የሚታይባቸው እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ሊያበሳጩንና የአእምሮ እረፍት ሊነሱን ይችላሉ። ክፉዎች የተሳካላቸው መስለው መታየታቸው የቅንዓት ስሜት ሊያሳድርብንም ይችላል። ሆኖም የእኛ መናደድ በሁኔታው ላይ የሚያመጣው ለውጥ ይኖራል? ክፉዎች ባገኙት ስኬት መቅናት አካሄዳቸው በሚያስከትልባቸው መዘዝ ላይ የሚያመጣው ለውጥ አለ? ምንም ለውጥ አያመጣም! ደግሞም ‘የምንበሳጭበት’ ምክንያት የለም። ለምን?
-
-
‘በይሖዋ ደስ ይበላችሁ’መጠበቂያ ግንብ—2003 | ታኅሣሥ 1
-
-
6. ከመዝሙር 37:1, 2 የምናገኘው ትምህርት ምንድን ነው?
6 ታዲያ ክፉዎች ባገኙት እርባና የሌለው ብልጽግና መናደድ ይኖርብናል? ከመዝሙር 37 የመጀመሪያ ሁለት ቁጥሮች የምናገኘው ትምህርት አለ:- እነርሱ ያገኙት ስኬት ይሖዋን ለማገልገል ከመረጥከው ጎዳና እንዲያስወጣህ አትፍቀድ። ከዚህ ይልቅ ትኩረትህን በመንፈሳዊ በረከቶችና ግቦች ላይ አድርግ።—ምሳሌ 23:17
-