የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ዓላማውን እንደሚፈጽም ሙሉ እምነት ይኑራችሁ
    መጠበቂያ ግንብ—1994 | መጋቢት 15
    • 15. ዳዊት በይሖዋ ዓላማ መተማመኑን የገለጸው እንዴት ነበር?

      15 ኢዮብ ከኖረበት ከስድስት መቶ ዘመናት በኋላና ኢየሱስ ወደ ምድር ከመምጣቱ ከአንድ ሺህ ዓመት በፊት ዳዊት አዲስ ዓለም እንደሚመጣ ያለውን ሙሉ እምነት ገልጿል። በመዝሙሮቹ ውስጥ እንደዚህ ብሏል፦ “እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ። ገና ጥቂት፣ ኃጢአተኛም አይኖርም፤ . . . ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፣ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል። ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፣ በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ።” ዳዊት የማይናወጥ ተስፋ ስለነበረው “በእግዚአብሔር ታመን፣ . . . በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፣ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል” በማለት አጥብቆ መክሯል።—መዝሙር 37:3, 4, 9–11, 29

  • ይሖዋ ዓላማውን እንደሚፈጽም ሙሉ እምነት ይኑራችሁ
    መጠበቂያ ግንብ—1994 | መጋቢት 15
    • 22. በይሖዋ ልንተማመን የሚገባን ለምንድን ነው?

      22 በአዲሱ ዓለም ታማኝ የሰው ዘሮች “ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው” የሚለው የሮሜ 8:21 ትንቢት ሲፈጸም ይመለከታሉ። ኢየሱስ ተከታዮቹን “መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን” ብለው እንዲጸልዩ ያስተማራቸው ጸሎት መልስ ሲያገኝ ይመለከታሉ። (ማቴዎስ 6:10) እንግዲያው “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፣ በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ” የሚል የማይታበል ተስፋ ስለሰጠን በይሖዋ ላይ ሙሉ በሙሉ እንታመን።—መዝሙር 37:29

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ