-
ለነጠላ ወላጆች አሳቢነት አሳይመጠበቂያ ግንብ—2010 | ታኅሣሥ 1
-
-
አሳቢነት ማሳየትህ ለአንተም ደስታ ያመጣልሃል። በጣም ከባድ የሆነ ሸክም የተሸከመ ሰው አጋጥሞህ ያገዝክበት ጊዜ አለ? ከሆነ ተግባራዊ በሆነ መንገድ እርዳታ በመስጠትህ ሳትደሰት አትቀርም። በተመሳሳይም ነጠላ ወላጆች ያለባቸው ኃላፊነት አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው ብቻውን ሊሸከመው የማይችለው ከባድ ሸክም ሊሆን ይችላል። ለእነሱ የእርዳታ እጅህን ስትዘረጋ በመዝሙር 41:1 (NW) ላይ የሚገኘውን “ለተቸገረ ሰው አሳቢነት የሚያሳይ ደስተኛ ነው” የሚለውን ሐሳብ እውነተኝነት ትገነዘባለህ።
-
-
ለነጠላ ወላጆች አሳቢነት አሳይመጠበቂያ ግንብ—2010 | ታኅሣሥ 1
-
-
እርዳታ ለማድረግ ቀላሉ መንገድ “ልረዳሽ የምችለው ነገር አለ?” ብሎ መጠየቅ ሊመስል ይችላል። ይሁንና እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ እንዲህ ብለህ መጠየቅህ የሚያስፈልጋትን ነገር በግልጽ እንድትናገር ላያደርጋት ይችላል። ቀደም ሲል እንደተመለከትነው በመዝሙር 41:1 ላይ ‘አሳቢነት እንድናሳይ’ ተመክረናል። አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ እንደገለጸው ይህን ሐሳብ ለማመልከት የገባው የዕብራይስጥ ሐረግ “ጥበብ የሚንጸባረቅበት አንድ እርምጃ ላይ መድረስ እንዲቻል የተለያዩ ሐሳቦችን የማውጣትና የማውረድ ሂደት” የሚል ትርጉም ሊኖረው ይችላል።
-