የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ክብር የተጎናጸፈውን ንጉሥ ክርስቶስን አወድሱ!
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | የካቲት 15
    • ንጉሡ “ስለ እውነት” ሲል ይገሰግሳል

      11. ክርስቶስ “ስለ እውነት” ሲል የሚገሰግሰው እንዴት ነው?

      11 መዝሙር 45:4⁠ን አንብብ። ተዋጊው ንጉሥ ጦርነት የሚያውጀው ግዛቱን ለማስፋትና ሰዎችን ለማስገበር አይደለም። ከዚህ ይልቅ የተቀደሰ ዓላማ ይዞ የጽድቅ ጦርነት ያውጃል። “ስለ እውነት፣ ስለ ትሕትና ስለ ጽድቅ” ይገሰግሳል። ከሁሉ ይበልጥ ጥብቅና ሊቆምለት የሚገባው ታላቅ እውነት የይሖዋ አጽናፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነት ነው። ሰይጣን በይሖዋ ላይ ባመፀ ጊዜ የእሱን አገዛዝ ሕጋዊነት ተገዳድሯል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ አጋንንትም ሆኑ ሰዎች ይህን መሠረታዊ እውነት ሲቃረኑ ቆይተዋል። ይሖዋ የቀባው ንጉሥ የይሖዋን ሉዓላዊ አገዛዝ ትክክለኛነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማረጋገጥ እርምጃ የሚወስድበት ጊዜ ደርሷል።

      12. ንጉሡ “ስለ ትሕትና” ሲል የሚገሰግሰው እንዴት ነው?

      12 በተጨማሪም ንጉሡ “ስለ ትሕትና” ሲል ይገሰግሳል። የአምላክ አንድያ ልጅ እንደመሆኑ መጠን እሱ ራሱ ትሕትና በማሳየትና ለአባቱ ሉዓላዊነት በታማኝነት በመገዛት ረገድ አቻ የማይገኝለት ምሳሌ ትቷል። (ኢሳ. 50:4, 5፤ ዮሐ. 5:19) የንጉሡ ታማኝ ተገዢዎች ሁሉ የእሱን ምሳሌ መከተልና በሁሉም ረገድ ለይሖዋ ሉዓላዊነት በትሕትና መገዛት ይኖርባቸዋል። አምላክ ቃል በገባው አዲስ ዓለም ውስጥ እንዲኖሩ የሚፈቀድላቸው እንዲህ ዓይነት ሰዎች ብቻ ናቸው።—ዘካ. 14:16, 17

      13. ክርስቶስ “ስለ ጽድቅ” ሲል የሚፋለመው እንዴት ነው?

      13 ከዚህም ሌላ ክርስቶስ ለጽድቅ ሲል ይፋለማል። ንጉሡ ጥብቅና የሚቆምለት ጽድቅ “የአምላክ ጽድቅ” ይኸውም ይሖዋ ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር በተመለከተ ያወጣው መሥፈርት ነው። (ሮም 3:21፤ ዘዳ. 32:4) ኢሳይያስ ንጉሡን ኢየሱስ ክርስቶስን አስመልክቶ “ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል” ሲል ትንቢት ተናግሯል። (ኢሳ. 32:1) የኢየሱስ አገዛዝ በተስፋ ሲጠበቁ የቆዩትን “አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር” የሚያመጣ ሲሆን “በእነዚህም ውስጥ ጽድቅ ይሰፍናል።” (2 ጴጥ. 3:13) በዚያ አዲስ ዓለም ውስጥ የሚኖር ሰው ሁሉ ከይሖዋ መሥፈርቶች ጋር ተስማምቶ መኖር ይጠበቅበታል።—ኢሳ. 11:1-5

      ንጉሡ “ድንቅ ተግባር” ያከናውናል

      14. የክርስቶስ ቀኝ እጅ “ድንቅ ተግባር” የሚያከናውነው እንዴት ነው? (በመግቢያው ላይ ያለውን ሥዕል ተመልከት።)

      14 ንጉሡ ሰይፍ በወገቡ ታጥቆ ይገሰግሳል። (መዝ. 45:3) ይሁንና ሰይፉን በቀኝ እጁ መዞ የሚጠቀምበት ጊዜ ይመጣል። መዝሙራዊው “ቀኝ እጅህም ድንቅ ተግባር ታሳይ” በማለት ትንቢት ተናግሯል። (መዝ. 45:4) ኢየሱስ ክርስቶስ በአርማጌዶን የይሖዋን ፍርድ ለማስፈጸም ሲገሰግስ በጠላቶቹ ላይ “ድንቅ ተግባር” ይፈጽማል። የሰይጣንን ሥርዓት ለማጥፋት የሚጠቀምበትን መሣሪያ በተመለከተ የምናውቀው ነገር የለም። ይሁንና ይህ እርምጃ ለንጉሡ አገዛዝ እንዲገዙ የተሰጣቸውን መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ችላ ያሉትን የምድር ነዋሪዎች ልብ ማሸበሩ አይቀርም። (መዝሙር 2:11, 12⁠ን አንብብ።) ኢየሱስ ስለ ፍጻሜው ዘመን በተናገረው ትንቢት ላይ “የሰማያት ኃይላት ስለሚናወጡ ሰዎች ከፍርሃትና በዓለም ላይ የሚመጡትን ነገሮች ከመጠበቅ የተነሳ ይዝለፈለፋሉ” ሲል ገልጿል። አክሎም ሲናገር “በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል” ብሏል።—ሉቃስ 21:26, 27

      15, 16. ክርስቶስ ለውጊያ ሲወጣ የሚከተለው “ሠራዊት” እነማንን ያካትታል?

      15 የራእይ መጽሐፍ ንጉሡ የፍርድ እርምጃ ለመውሰድ “በኃይልና በታላቅ ክብር” እንደሚመጣ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ “እኔም ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም፣ ነጭ ፈረስ ነበር። በእሱም ላይ የተቀመጠው ‘የታመነና እውነተኛ’ ተብሎ ይጠራል፤ እሱም በጽድቅ ይፈርዳል እንዲሁም ይዋጋል። በተጨማሪም በሰማይ ያሉት ሠራዊት በነጭ ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር፤ እነሱም ነጭና ንጹሕ የሆነ ጥሩ በፍታ ለብሰው ነበር። ብሔራትን ይመታበት ዘንድ ከአፉ ረጅም ስለታም ሰይፍ ይወጣል፤ እንደ እረኛም በብረት በትር ያግዳቸዋል። በተጨማሪም ሁሉን ቻይ የሆነውን የአምላክን የመዓቱን የቁጣ ወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል።”—ራእይ 19:11, 14, 15

      16 ከክርስቶስ ጋር አብረው ለውጊያ የሚዘምቱት የሰማይ “ሠራዊት” አባላት የሆኑ ተዋጊዎች እነማን ናቸው? ኢየሱስ ሰይጣንንና አጋንንቱን ከሰማይ ለማባረር ለመጀመሪያ ጊዜ ሰይፉን ሲታጠቅ “መላእክቱ” አብረውት ነበሩ። (ራእይ 12:7-9) በአርማጌዶን ጦርነት ወቅት የክርስቶስ ሠራዊት ቅዱሳን መላእክትን ያቀፈ ይሆናል ብሎ መጠበቁ ምክንያታዊ ነው። ሠራዊቱ ሌሎችንም ያካትት ይሆን? ኢየሱስ ለተቀቡት ወንድሞቹ እንዲህ ሲል ቃል ገብቷል፦ “ድል ለሚነሳና በሥራዬ እስከ መጨረሻ ለሚጸናም በሕዝቦች ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ፤ እሱም ሕዝቦችን እንደ ሸክላ ዕቃ እንዲደቁ እንደ እረኛ በብረት በትር ያግዳቸዋል፤ ይህም እኔ ከአባቴ ሥልጣን እንደተቀበልኩት ዓይነት ነው።” (ራእይ 2:26, 27) ስለዚህ በሰማይ ያለው የክርስቶስ ሠራዊት የተቀቡ ወንድሞቹን ያካትታል፤ በዚያን ጊዜ የክርስቶስ ወንድሞች ሰማያዊ ሽልማታቸውን ተቀብለው እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ኢየሱስ ብሔራትን እንደ እረኛ በብረት በትር በሚያግድበትና “ድንቅ ተግባር” በሚያከናውንበት ጊዜ የተቀቡት ተባባሪ ገዢዎች ከእሱ ጎን ይሰለፋሉ።

  • ክብር የተጎናጸፈውን ንጉሥ ክርስቶስን አወድሱ!
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | የካቲት 15
    • 19. ክርስቶስ ‘በድል አድራጊነት የሚገሰግሰውና’ ድሉን የሚያጠናቅቀው እንዴት ነው?

      19 ክርስቶስ የሰይጣንን ክፉ ሥርዓት ከምድር ገጽ ካጠፋ በኋላ ‘ሞገስ ተጎናጽፎ በድል አድራጊነት ይገሰግሳል።’ (መዝ. 45:4) ለሺህ ዓመት በሚቆየው የግዛት ዘመን ሰይጣንንና አጋንንቱን በጥልቁ ውስጥ በማሰር ድሉን ያጠናቅቃል። (ራእይ 20:2, 3) በዚያን ጊዜ ዲያብሎስና መላእክቱ የሞቱ ያህል ሆነው እንዳይንቀሳቀሱ ስለሚደረጉ የምድር ነዋሪዎች ከሰይጣን ተጽዕኖ የሚገላገሉ ከመሆኑም ሌላ ድል አድራጊ ለሆነውና ክብር ለተላበሰው ንጉሣቸው ፍጹም ተገዢ ሆነው ይኖራሉ። ይሁን እንጂ ምድር ሙሉ በሙሉ ወደ ገነትነት ተለውጣ ከማየታቸው በፊት ከንጉሣቸውና በሰማይ ካሉት ተባባሪዎቹ ጋር ሐሴት ለማድረግ የሚያስችል ተጨማሪ ምክንያት ይኖራቸዋል። ይህ አስደሳች ክንውን በሚቀጥለው ርዕስ ላይ ይብራራል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ