የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በበጉ ሠርግ ደስ ይበላችሁ!
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | የካቲት 15
    • 6. ቅቡዓኑ “የንጉሥ ልጅ” ተብለው የተጠሩት ለምንድን ነው? ‘ሕዝባቸውን እንዲረሱ’ የተመከሩትስ ለምንድን ነው?

      6 ዕጩዋ ሙሽራ “ልጄ ሆይ” ተብላ ከመጠራቷም ሌላ “የንጉሥ ልጅ” ተብላለች። (መዝ. 45:13) ይህ “ንጉሥ” ማን ነው? ቅቡዓን ክርስቲያኖች የይሖዋ “ልጆች” የመሆን መብት አግኝተዋል። (ሮም 8:15-17) ቅቡዓኑ በሰማይ ሙሽራ ስለሚሆኑ ‘ሕዝባቸውንና [የሥጋዊ] አባታቸውን ቤት’ እንዲረሱ ተመክረዋል። አእምሯቸው “በምድር ባሉት ነገሮች ላይ ሳይሆን ምንጊዜም በላይ ባሉት ነገሮች ላይ እንዲያተኩር” ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።—ቆላ. 3:1-4

  • በበጉ ሠርግ ደስ ይበላችሁ!
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | የካቲት 15
    • ሙሽራዋ ‘ወደ ንጉሡ ትወሰዳለች’

      8. ሙሽራዋ ‘ከላይ እስከ ታች እንደተሸለመች’ ተደርጋ መገለጿ ተስማሚ የሆነው ለምንድን ነው?

      8 መዝሙር 45:13, 14ሀን አንብብ። ሙሽራዋ ለንጉሣዊው ሠርግ “ከላይ እስከ ታች ተሸልማ” ተዘጋጅታለች። ራእይ 21:2 ላይ ሙሽራዋ በአንዲት ከተማ ይኸውም በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ተመስላ የተገለጸች ሲሆን ‘ለባሏ አጊጣለች።’ ይህች ሰማያዊት ከተማ “የአምላክን ክብር” የተላበሰች ከመሆኑም ሌላ ብርሃኗ “እጅግ እንደከበረ ድንጋይ፣ እንደ ኢያስጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ክሪስታል ጥርት ብሎ [ያንጸባርቃል]።” (ራእይ 21:10, 11) አዲሲቱ ኢየሩሳሌም የተላበሰችው ዕፁብ ድንቅ የሆነ ውበት በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ማራኪ በሆነ መንገድ ተገልጿል። (ራእይ 21:18-21) መዝሙራዊው፣ ሙሽራዋ ‘ከላይ እስከ ታች እንደተሸለመች’ አድርጎ መግለጹ ምንም አያስገርምም! ደግሞም የንጉሡ ሠርግ የሚከናወነው በሰማይ ነው።

      9. ሙሽራዋ የምትወሰደው ወደ የትኛው “ንጉሥ” ነው? አለባበሷስ ምን ይመስላል?

      9 ሙሽራዋ የተወሰደችው ወደ ሙሽራው ይኸውም ወደ መሲሐዊው ንጉሥ ነው። “በቃሉ አማካኝነት በውኃ አጥቦ በማንጻት” ሲያዘጋጃት ቆይቷል። ሙሽራዋ “ቅዱስና እንከን የለሽ” ነች። (ኤፌ. 5:26, 27) በተጨማሪም ሙሽራዋ ለሠርጉ የሚስማማ አለባበስ ሊኖራት ይገባል። ደግሞም እጅግ ተውባለች! ‘ልብሷ ወርቀ ዘቦ’ ሲሆን ‘በጥልፍ ሥራ ባጌጠ ልብስ ወደ ንጉሡ ትወሰዳለች።’ ለበጉ ሠርግ “የሚያንጸባርቅና ንጹሕ የሆነ ጥሩ በፍታ እንድትጎናጸፍ ተሰጥቷታል፤ ምክንያቱም ይህ ጥሩ በፍታ የቅዱሳንን የጽድቅ ተግባር ያመለክታል።”—ራእይ 19:8

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ