የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር” በይሖዋ ተቆጥሯል
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ነሐሴ 1
    • ‘እንባዬን በአቊማዳህ አጠራቅም’

      12. ይሖዋ ሕዝቦቹ የሚደርስባቸውን ችግር በሚገባ እንደሚገነዘብ እንዴት መረዳት እንችላለን?

      12 ይሖዋ አገልጋዮቹን በግለሰብ ደረጃ ከማወቅም አልፎ ምን ችግር እየደረሰባቸው እንዳለ በሚገባ ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል እስራኤላውያን በባርነት ሲሰቃዩ ይሖዋ ለሙሴ እንዲህ ብሎት ነበር:- “በግብፅ አገር የሚኖሩትን የሕዝቤን መከራ አይቻለሁ፤ ከአሠሪዎቻቸው ጭካኔ የተነሣ የሚያሰሙትንም ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ሥቃያቸውንም ተረድቼአለሁ።” (ዘፀአት 3:7) ያጋጠመንን ችግር በጽናት ለመቋቋም ስንጣጣር ይሖዋ እንደሚመለከተንና ጩኸታችንንም እንደሚሰማ ማወቁ እንዴት ያጽናናል! ይሖዋ የሚደርስብንን ችግር ፈጽሞ በግድየለሽነት አይመለከትም።

      13. ይሖዋ በእርግጥ የአገልጋዮቹን ስሜት እንደሚጋራ የሚያሳየው ምንድን ነው?

      13 ይሖዋ ከእርሱ ጋር ወዳጅነት ለመሠረቱ ሰዎች ምን ያህል አሳቢ እንደሆነ ለእስራኤላውያን ከነበረው ስሜት ሰፊ ግንዛቤ ማግኘት ይቻላል። ብዙውን ጊዜ ለችግር ይዳርጋቸው የነበረው የራሳቸው አንገተ ደንዳናነት ቢሆንም፣ ኢሳይያስ “በጭንቃቸው ሁሉ ተጨነቀ” በማለት ስለ ይሖዋ ስሜት ተናግሯል። (ኢሳይያስ 63:9) የይሖዋ ታማኝ አገልጋይ እንደመሆንህ መጠን፣ ሥቃይ በሚደርስብህ ጊዜ እርሱም አብሮህ እንደሚሠቃይ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። ይህን ማወቅህ የሚያጋጥሙህን መከራዎች ያለ ፍርሃት እንድትጋፈጥና አቅምህ በፈቀደው ሁሉ ይሖዋን ማገልገልህን እንድትቀጥል አላነሳሳህም?—1 ጴጥሮስ 5:6, 7

      14. መዝሙር 56 በተቀናበረበት ወቅት ሁኔታዎቹ ምን ይመስሉ ነበር?

      14 ዳዊት፣ ይሖዋ እንደሚያስብለትና በሥቃዩ ጊዜ አብሮት እንደሚሠቃይ እምነት እንደነበረው መዝሙር 56 ያሳያል። ዳዊት ይህንን መዝሙር ያቀናበረው ሊገድለው ከሚፈልገው ከንጉሥ ሳኦል ፊት በመሸሽ ላይ በነበረበት ወቅት ነው። በዚህ ጊዜ ዳዊት ወደ ጌት ሸሽቶ ሄዶ ነበር፤ ይሁንና ፍልስጥኤማውያን ማንነቱን በማወቃቸው ምክንያት እንዳይዙት ፍራቻ አደረበት። ዳዊት “ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ፤ በትዕቢት የሚዋጉኝ ብዙዎች ናቸውና” በማለት ጽፏል። የነበረበት ሁኔታ አደገኛ በመሆኑ ምክንያት ፊቱን ወደ ይሖዋ አዞረ። እንዲህ ብሎ ነበር:- “ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምሙታል፤ ዘወትርም ሊጐዱኝ ያሤራሉ።”—መዝሙር 56:2, 5

      15. (ሀ) ዳዊት እንባውን በአቁማዳው እንዲያጠራቅምለት ወይም ደግሞ በመዝገቡ እንዲይዝለት ይሖዋን ሲጠይቅ ምን ማለቱ ነበር? (ለ) እምነትን ከሚፈታተን ሁኔታ ጋር እየታገልን ከሆነ ስለ ምን ነገር እርግጠኞች መሆን እንችላለን?

      15 ዳዊት በመዝሙር 56:8 ላይ የሚከተሉትን ትኩረት የሚስቡ ቃላት ተናግሯል:- “ሰቆቃዬን መዝግብ፤ እንባዬን በዕቃህ [‘በአቊማዳህ፣’ የግርጌ ማስታወሻ] አጠራቅም፤ ሁሉስ በመዝገብህ የተያዘ አይደለምን?” የይሖዋን ፍቅራዊ አሳቢነት የሚያሳይ እንዴት ያለ መግለጫ ነው! በውጥረት ውስጥ ስንሆን ለይሖዋ ከእንባ ጋር ልመና ማቅረብ እንችላለን። ፍጹም ሰው የነበረው ኢየሱስ እንኳን እንዲህ አድርጎ ነበር። (ዕብራውያን 5:7) ዳዊት፣ ይሖዋ እንባውን በአቁማዳ ያጠራቀመለት ያህል ወይም ደግሞ በመዝገብ ያሰፈረለት ያህል እንደሚከታተለውና ሥቃዩን እንደሚያስታውስ እምነት ነበረው።d ምናልባት የአንተ እንባ ያን አቁማዳ እንደሚሞላው ወይም የመዝገቡን በርካታ ገጾች እንደሚይዝ ሆኖ ሊሰማህ ይችላል። እንዲህ የሚሰማህ ከሆነ መጽናኛ ማግኘት ትችላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል” የሚል ማረጋገጫ ይሰጠናል።—መዝሙር 34:18

  • “የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር” በይሖዋ ተቆጥሯል
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ነሐሴ 1
    • d በጥንት ዘመን የበግ፣ የፍየልና የከብት ቆዳ በማልፋት አቁማዳ ይዘጋጅ ነበር። አቁማዳ ለወተት፣ ለቅቤ፣ ለአይብ ወይም ለውኃ መያዣነት ያገለግል ነበር። ቆዳው በደንብ ከለፋ ደግሞ ዘይት ወይም ወይን ጠጅ መያዝ ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ