የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • እርዳታ ለማግኘት የሚጮኹትን የሚታደገው ማነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 15
    • 14, 15. ኢየሱስ የሰዎችን ስሜት እንደሚረዳና ‘ችግረኛው በጮኸ ጊዜ እንደሚታደገው’ እንዴት ማወቅ እንችላለን?

      14 ኃጢአተኛ የሆኑ የሰው ልጆች በአሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ስለሚገኙ በእጅጉ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይሁንና ከዚህ አሳዛኝ ሁኔታ መገላገል እንደምንችል ተስፋ አለን። (መዝሙር 72:12-14⁠ን አንብብ።) ታላቁ ሰለሞን ኢየሱስ ፍጽምና በጎደለው ሁኔታ ውስጥ እንደምንኖር ስለሚገነዘብ ይራራልናል። ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ ለጽድቅ ሲል ሥቃይ የደረሰበት ሲሆን አምላክም ኢየሱስ የደረሰበትን መከራ በራሱ እንዲወጣ ፈቅዷል። እንዲያውም ኢየሱስ ‘ላቡ ወደ ምድር እንደሚንጠባጠብ የደም ነጠብጣብ’ እስኪሆን ድረስ ከፍተኛ የስሜት ሥቃይ ደርሶበት ነበር። (ሉቃስ 22:44) በመከራ እንጨት ላይ በተሰቀለበት ጊዜም “አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮዃል። (ማቴ. 27:45, 46) ኢየሱስ ይህ ሁሉ ሥቃይ ቢደርስበትም እንዲሁም ሰይጣን ይሖዋን እንዲተው ለማድረግ የተቻለውን ሁሉ ጥረት ቢያደርግም እንኳ ኢየሱስ ለይሖዋ አምላክ ታማኝ መሆኑን አስመሥክሯል።

  • እርዳታ ለማግኘት የሚጮኹትን የሚታደገው ማነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 15
    • 16. ሰለሞን ለተገዥዎቹ እንዲያዝን ያደረገው ምን ሊሆን ይችላል?

      16 ሰለሞን ጥበብና ማስተዋል ስለነበረው “ለችግረኞች ይራራ” እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም። ከዚህም በላይ የእሱ ሕይወት በሐዘንና በአሰቃቂ ሁኔታዎች የተሞላ ነበር። ወንድሙ አምኖን እህቱን ትዕማርን የደፈራት ሲሆን አቤሴሎም ደግሞ ወንድሙ በፈጸመው ወንጀል ምክንያት አምኖንን ገድሎታል። (2 ሳሙ. 13:1, 14, 28, 29) አቤሴሎም የዳዊትን ዙፋን ለመገልበጥ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም ሙከራው ከሽፎ በኢዮአብ ተገድሏል። (2 ሳሙ. 15:10, 14፤ 18:9, 14) ከጊዜ በኋላ የሰለሞን ወንድም አዶንያስ ዙፋኑን ለመውረስ ሞክሮ ነበር። አዶንያስ ቢሳካለት ኖሮ ሰለሞንን እንደሚያስገድለው ምንም ጥርጥር አልነበረውም። (1 ነገ. 1:50) ሰለሞን የይሖዋ ቤተ መቅደስ በተመረቀ ጊዜ ባቀረበው ጸሎት ላይ የተናገረው ሐሳብ በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰውን ሥቃይ እንደሚረዳ በግልጽ ያሳያል። ንጉሡ ተገዥዎቹን አስመልክቶ ወደ ይሖዋ ሲጸልይ እንዲህ ብሏል፦ ‘ማንም ሰው ጭንቀቱና ሕመሙ ተሰምቶት ጸሎትና ልመና ቢያቀርብ ይቅር በል፤ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው መጠን ክፈለው።’—2 ዜና 6:29, 30

      17, 18. አንዳንድ የአምላክ አገልጋዮች ምን ዓይነት ‘ጭንቀትና ሕመም’ መቋቋም ግድ ሆኖባቸዋል? እንዲቋቋሙ የረዳቸውስ ምንድን ነው?

      17 ምናልባትም እኛ ‘ጭንቀትና ሕመም’ የሚሰማን ከዚህ በፊት በሕይወታችን ውስጥ ባጋጠመን አሳዛኝ ሁኔታ ምክንያት ሊሆን ይችላል። በ30ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የምትገኘው ሜሪa የምትባል አንዲት የይሖዋ ምሥክር እንዲህ ብላለች፦ “ደስተኛ መሆን የምችልበት በቂ ምክንያት አለኝ፤ ሆኖም በሕይወቴ ውስጥ ያጋጠመኝ ሁኔታ ብዙ ጊዜ የኀፍረት ስሜት እንዲሰማኝና ራሴን እንድጠላ ያደርገኛል። በዚህ ጊዜ ከፍተኛ የሐዘን ስሜት ስለሚሰማኝ ልክ ሁሉ ነገር ትናንትና የተፈጸመብኝ ይመስል ለማልቀስ ይዳዳኛል። ፈጽሞ ከአእምሮዬ ሊጠፋ ያልቻለው መጥፎ ትዝታ አሁንም የከንቱነትና የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማኝ ያደርገኛል።”

      18 በርካታ የአምላክ አገልጋዮች እንዲህ ዓይነት ስሜት ይሰማቸዋል፤ ሆኖም እንዲህ ያለውን ስሜት ተቋቁመው ለመጽናት የሚያስችላቸውን ብርታት እንዲያገኙ ምን ሊረዳቸው ይችላል? ሜሪ እንዲህ ብላለች፦ “እውነተኛ ወዳጆቼና መንፈሳዊ ቤተሰቦቼ ደስተኛ እንድሆን ረድተውኛል። እኔም ብሆን ይሖዋ ስለወደፊቱ ጊዜ በሰጠው ተስፋ ላይ ትኩረት ለማድረግ እሞክራለሁ፤ እንዲሁም በዚያን ጊዜ እርዳታ ለማግኘት የማሰማው ጩኸት ወደ ደስታ ጩኸት እንደሚለወጥ እርግጠኛ ነኝ።” (መዝ. 126:5) ተስፋችንን አምላክ በሾመው ገዥ በልጁ በኢየሱስ ላይ ማድረግ ይኖርብናል። እሱን በሚመለከት እንዲህ የሚል ትንቢት ተነግሯል፦ “ለድኾችና ለችግረኞች ይራራል፤ ምስኪኖችንም ከሞት ያድናል። ሕይወታቸውን ከጭቈናና ከግፍ ያድናል፤ ደማቸውም በእርሱ ፊት ክቡር ነው።” (መዝ. 72:13, 14) ይህ እንዴት የሚያጽናና ነው!

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ