የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 5/15 ገጽ 32
  • ‘አምላክ መጠጊያዬ ነው’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘አምላክ መጠጊያዬ ነው’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 5/15 ገጽ 32

‘አምላክ መጠጊያዬ ነው’

በዚህ ‘አስጨናቂ ዘመን’ ፈተናዎችና ተጽዕኖዎች ከመቼውም ጊዜ ይልቅ እያየሉ መጥተዋል። ለምሳሌ ያህል በሥራ ቦታ ሐቀኝነታችን ሊፈተን ይችላል። አብረናቸው የምንማር ተማሪዎች የሥነ ምግባር ንጽሕናችንን አደጋ ላይ ሊጥሉት ይችላሉ። በሥነ ምግባር ያዘቀጠው ዓለም በአቋም ጽናታችን ላይ ዘወትር ፈተና ያመጣብናል።​— 2 ጢሞቴዎስ 3:​1-5

የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የነበረው አሳፍም ክፋት ተንሰራፍቶ በነበረበት ዘመን ኖሯል። እንዲያውም በጊዜው ይኖሩ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ለአምላክ አክብሮት በማያመጣው ድርጊታቸው ይኩራሩ ነበር። “ትዕቢትን እንደ ድሪ አጥልቀዋል” በማለት አሳፍ ጽፏል። “ዐመፅንም እንደ ልብስ ለብሰዋል። በሌሎች ሰዎች ላይ ይስቃሉ፤ ክፉ ነገርም ይናገራሉ፤ ትምክሕተኞች ናቸው፤ ሌሎችንም ለመጨቆን ይነሳሉ።” (መዝሙር 73:​6, 8 የ1980 ትርጉም) እንዲህ ያለው ዝንባሌ የተለመደ ነው?

ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ የሚመኙ ሰዎች እንደዚህ ዓይነቱ ተግባር በጣም ያሳዝናቸዋል፤ እንዲያውም ተስፋ ያስቆርጣቸዋል። “ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ” በማለት አሳፍ በምሬት ተናግሯል። “በፊቴ ችግር ነበር።” (መዝሙር 73:​14, 16) አንተም እንዲሁ ይሰማህ ይሆናል። ቢሆንም ተስፋ አትቁረጥ! አሳፍ በዘመኑ የነበረውን ክፋት በአሸናፊነት መወጣት ችሎ ነበር። አንተም እንዲሁ ማድረግ ትችላለህ። ግን እንዴት?

አሳፍ ከፍጽምና ከራቀው የሰው አገዛዝ እውነተኛ ፍትሕ ሊገኝ እንደማይችል ተገንዝቧል። (መዝሙር 146:​3, 4፤ ምሳሌ 17:​23) ስለዚህ የከበቡትን ክፉ ድርጊቶች ለማስወገድ በመሞከር ውድ ጊዜውን፣ ኃይሉንና ጥሪቱን ከማባከን ይልቅ ከአምላክ ጋር በነበረው ዝምድና ላይ አተኩሯል። አሳፍ “ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው” በማለት ገልጿል።​— መዝሙር 73:​28

ዛሬም ብልሹ በሆነው የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ቁሳዊ ንብረቶችን ያካብታሉ። እንዲያውም ብዙዎች የአምላክን የሥነ ምግባር ሕግጋት ችላ በማለታቸው ይኩራራሉ። ይሁን እንጂ በዚህ ሁኔታ ለዘላለም አይቀጥሉም። አሳፍ “በድጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው” በማለት ያስተዋለ​ውን ጽፏል። “ወደ ጥፋትም ጣልኻቸው።”​— መዝሙር 73:​18

አዎን፣ እውነተኛ ክርስቲያኖች ሊርቋቸው የሚገባቸው አታላይነት፣ ዓመፅና ሙስና እንዲሁም ሌሎች ለአምላክ ክብር የማያመጡ ድርጊቶች ሁሉ አምላክ በወሰነው ጊዜ ተጠራርገው ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ “ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ” በማለት ተስፋ ይሰጣል። (መዝሙር 37:​9) እስከዚያው ጊዜ ግን “እግዚአብሔር ዓለቴ፣ አምባዬ፣ መድኃኒቴ፣ አምላኬ፣ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፣ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው” ብሎ የተናገረውን የመዝሙራዊውን ቃላት እናስተጋባ።​— መዝሙር 18:​2

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ