የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋ ይቅርታ ወደር የለውም
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022 | ሰኔ
    • የይሖዋ ይቅርታ ወደር የለውም

      “ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጥሩ ነህና፤ ይቅር ለማለትም ዝግጁ ነህ፤ አንተን ለሚጠሩ ሁሉ የምታሳየው ታማኝ ፍቅር ወሰን የለውም።”—መዝ. 86:5

  • የይሖዋ ይቅርታ ወደር የለውም
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022 | ሰኔ
    • ይሖዋ ይቅር ለማለት ዝግጁ ነው

      4. ይሖዋ ይቅር ለማለት ዝግጁ እንደሆነ እርግጠኞች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

      4 የአምላክ ቃል ይሖዋ ይቅር ለማለት ዝግጁ እንደሆነ ያረጋግጥልናል። ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ ራሱን ለሙሴ በገለጠበት ወቅት በአንድ መልአክ አማካኝነት እንዲህ ብሎ ነበር፦ “ይሖዋ፣ ይሖዋ፣ መሐሪና ሩኅሩኅ የሆነ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየ፣ ታማኝ ፍቅሩና እውነቱ እጅግ ብዙ የሆነ፣ ታማኝ ፍቅርን ለሺዎች የሚያሳይ፣ ስህተትን፣ መተላለፍንና ኃጢአትን ይቅር የሚል።” (ዘፀ. 34:6, 7) ይሖዋ ንስሐ የሚገቡ ኃጢአተኞችን ይቅር ለማለት ምንጊዜም ዝግጁ የሆነ ደግና መሐሪ አምላክ ነው።—ነህ. 9:17፤ መዝ. 86:15

      በመዝሙር 103:13, 14 ላይ የሚገኘው “እሱ እንዴት እንደተሠራን በሚገባ ያውቃል” የሚለው ጥቅስ ከአንዲት እህት አጠገብ አለ። ከልጅነቷ ጀምሮ የነበራትን ሕይወት የሚያሳዩ ፎቶግራፎች በዙሪያዋ ይታያሉ።

      ይሖዋ ማንነታችንን የቀረጹትን ነገሮች በሙሉ ያውቃል (አንቀጽ 5⁠ን ተመልከት)

      5. በመዝሙር 103:13, 14 መሠረት ይሖዋ ሰዎችን በጥልቀት ማወቁ ምን እንዲያደርግ ያነሳሳዋል?

      5 ይሖዋ ፈጣሪያችን ስለሆነ ስለ እኛ ሁሉንም ነገር ያውቃል። እስቲ አስበው! በምድር ላይ ስላለው ስለ እያንዳንዱ ሰው እያንዳንዷን ዝርዝር ነገር ያውቃል። (መዝ. 139:15-17) ስለዚህ ከወላጆቻችን የወረስነውን አለፍጽምና በሙሉ ማየት ይችላል። በተጨማሪም በሕይወታችን ውስጥ ያጋጠሙን ነገሮች ባሕርያችንን የቀረጹት እንዴት እንደሆነ ያውቃል። ይሖዋ የሰው ልጆችን እንዲህ በጥልቀት ማወቁ ምን እንዲያደርግ ያነሳሳዋል? በምሕረት እንዲይዘን ያነሳሳዋል።—መዝ. 78:39፤ መዝሙር 103:13, 14⁠ን አንብብ።

      6. ይሖዋ እኛን ይቅር የማለት ጉጉት እንዳለው በተግባር ያሳየው እንዴት ነው?

      6 ይሖዋ ይቅር ለማለት እንደሚጓጓ በተግባር አሳይቷል። የመጀመሪያው ሰው አዳም በሠራው ኃጢአት የተነሳ ሁላችንም በኃጢአትና በሞት እርግማን ሥር እንደወደቅን ያውቃል። (ሮም 5:12) ራሳችንንም ሆነ ሌላ ማንኛውንም ሰው ከዚህ እርግማን ማላቀቅ የምንችልበት ምንም መንገድ አልነበረም። (መዝ. 49:7-9) ያም ቢሆን አፍቃሪ የሆነው አምላካችን ነፃ የምንወጣበትን መንገድ በማዘጋጀት ርኅራኄ አሳይቶናል። በምን መንገድ? ዮሐንስ 3:16 እንደሚገልጸው ይሖዋ አንድያ ልጁን ለእኛ ሲል እንዲሞት ላከልን። (ማቴ. 20:28፤ ሮም 5:19) ኢየሱስ በእሱ የሚያምን ሁሉ ነፃ መውጣት እንዲችል በእኛ ምትክ የሞትን ቅጣት ተቀበለ። (ዕብ. 2:9) ይሖዋ የሚወደው ልጁ ተሠቃይቶና ተዋርዶ ሲሞት ሲያይ ምንኛ አዝኖ ይሆን! ይሖዋ እኛን ይቅር የማለት ፍላጎት ባይኖረው ኖሮ ልጁ እንዲሞት አይፈቅድም ነበር።

      7. ይሖዋ በነፃ ይቅር ካላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች መካከል አንዳንዶቹን ጥቀስ።

      7 ይሖዋ በነፃ ይቅር ያላቸው በርካታ ሰዎች ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል። (ኤፌ. 4:32) የማንን ታሪክ ታስታውሳለህ? ንጉሥ ምናሴን ታስታውስ ይሆናል። ይህ ክፉ ሰው ዘግናኝ ኃጢአቶችን በመሥራት ይሖዋን አሳዝኗል። የሐሰት አምልኮን አስፋፍቷል። የገዛ ልጆቹን እንኳ ለሐሰት አማልክት መሥዋዕት አድርጎ አቅርቧል። ይባስ ብሎም ቅዱስ በሆነው የይሖዋ ቤተ መቅደስ ውስጥ ጣዖት አቁሟል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እሱ ሲናገር “ይሖዋን ያስቆጣው ዘንድ በእሱ ፊት በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮችን ሠራ” ይላል። (2 ዜና 33:2-7) ሆኖም ምናሴ ከልቡ ንስሐ ስለገባ ይሖዋ በነፃ ይቅር ብሎታል። እንዲያውም ወደ ንግሥናው እንዲመለስ አድርጎታል። (2 ዜና 33:12, 13) ምናልባት የንጉሥ ዳዊትን ታሪክም ታስታውስ ይሆናል። ንጉሥ ዳዊት እንደ ምንዝርና ነፍስ ግድያ ያሉ ከባድ ኃጢአቶችን በመሥራት ይሖዋን አሳዝኗል። ሆኖም ዳዊት ኃጢአቱን አምኖ ተቀብሎ ከልቡ ንስሐ ስለገባ ይሖዋ በነፃ ይቅር ብሎታል። (2 ሳሙ. 12:9, 10, 13, 14) በእርግጥም ይሖዋ ይቅር ለማለት እንደሚጓጓ መተማመን እንችላለን። ደግሞም ቀጥሎ እንደምንመለከተው ይሖዋ የሚያሳየው ይቅርታ ሰዎች ከሚያሳዩት ይቅርታ በእጅጉ የተለየ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ