የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ዕድሜያችንን እንዴት እንደምንቆጥር ያስተምረናል
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ኅዳር 15
    • 4-6. ይሖዋ እውነተኛ ‘መጠጊያ’ የሆነልን እንዴት ነው?

      4 መዝሙራዊው በሚከተሉት ቃላት ይከፍታል:- “እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ሆንህልን። ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣ ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣ አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ።”​—⁠መዝሙር 90:1, 2 አ.መ.ት

  • ይሖዋ ዕድሜያችንን እንዴት እንደምንቆጥር ያስተምረናል
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ኅዳር 15
    • 7. ተራሮች ‘የተወለዱት’ ምድርም ‘በምጥ’ የተገኘችው እንዴት ነው?

      7 ይሖዋ “ተራሮች ሳይወለዱ” ወይም ምድር “በምጥ” [NW ] ከመገኘቷ በፊት ይኖር ነበር። በሰው ዓይን ሲታይ ከተለያዩ ገጽታዎቿ፣ ኬሚካላዊ ዑደቶቿና እጅግ ውስብስብ ከሆኑት አሠራሯ ጋር ምድርን መፍጠር ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቅ ነው። መዝሙራዊው ተራሮች እንደ ‘ተወለዱ’ ምድርም ‘በምጥ’ እንደተገኘች አድርጎ መናገሩ ይሖዋ እነዚህን ነገሮች ሲፈጥር ምን ያህል ሥራ እንደጠየቀበት በመገንዘብ ለዚህ የፍጥረት ሥራ ያለውን ታላቅ አክብሮት መግለጹ ነበር። እኛስ ለፈጣሪ የእጅ ሥራዎች ተመሳሳይ የአክብሮትና የአድናቆት ስሜት ሊኖረን አይገባንም?

      ይሖዋ ምንጊዜም እኛን ለመርዳት ዝግጁ ነው

      8. ይሖዋ ‘ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነው’ የሚለው አባባል ምን ትርጉም አለው?

      8 መዝሙራዊው “አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ” በማለት ዘምሯል። “ዘላለም” የሚለው ቃል መጨረሻ ያላቸውን ሆኖም የሚቆዩበት የጊዜ ርዝመት በግልጽ ያልተቀመጠላቸውን ነገሮች ሊያመለክት ይችላል። (ዘጸአት 31:16, 17፤ ዕብራውያን 9:15) ሆኖም በመዝሙር 90:​2 እና በሌሎች የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ላይ የሚገኘው ‘ዘላለም’ የሚለው አገላለጽ “መጨረሻ የሌለው” የሚል ትርጉም አለው። (መክብብ 1:​4) አምላክ ለዘላለም የሚኖር ነው የሚለው አባባል ለአእምሯችን የሚከብድ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ይሖዋ መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ የለውም። (ዕንባቆም 1:12 NW ) ምንጊዜም ሕያውና እኛን ለመርዳት ዝግጁ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ