የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ዕድሜያችንን እንዴት እንደምንቆጥር ያስተምረናል
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ኅዳር 15
    • 17. አማካይ የሰዎች እድሜ ምን ያህል ነው? ዕድሜያችን በምን የተሞላ ነው?

      17 ፍጽምና የሌላቸውን የሰው ልጆች ዕድሜ ርዝመት በማስመልከት መዝሙራዊው እንዲህ ብሏል:- “የዕድሜአችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጉዳለን።” (መዝሙር 90:10 አ.መ.ት ) በአጠቃላይ ሲታይ የሰው እድሜ 70 ዓመት ገደማ ነው፤ ይሁንና ካሌብ በ85 ዓመቱ አስገራሚ ጥንካሬ እንደነበረው ተናግሯል። እንደ አሮን (123)፣ ሙሴ (120) እና ኢያሱ (110) ያሉ አንዳንድ ሰዎች ከተለመደው የዕድሜ ጣሪያ በላይ ኖረዋል። (ዘኁልቊ 33:39፤ ዘዳግም 34:7፤ ኢያሱ 14:6, 10, 11፤ 24:29) ይሁን እንጂ ከግብፅ ከወጣው እምነት የለሽ ትውልድ መካከል 20 እና ከዚያ በላይ እድሜ ያላቸው በ40 ዓመት ጊዜ ውስጥ ሞተው አልቀዋል። (ዘኁልቊ 14:29-34) በዛሬው ጊዜ በብዙ አገሮች የሰዎች አማካይ እድሜ መዝሙራዊው ከተናገረው ክልል አያልፍም። ዕድሜያችን ‘በድካምና በመከራ’ የተሞላ ነው። ቶሎ ያልፋል “እኛም ወዲያው እንነጉዳለን።”​—⁠ኢዮብ 14:1, 2

  • ይሖዋ ዕድሜያችንን እንዴት እንደምንቆጥር ያስተምረናል
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ኅዳር 15
    • 19 መዝሙራዊው የተናገራቸው ቃላት ሕዝቡ የቀረውን ዕድሜያቸውን በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ባለው መንገድ በጥበብ መመዘንና መጠቀም እንዲችሉ ይሖዋ እንዲያስተምራቸው የቀረበ ጸሎት ነው። ሰባ ዓመት አማካይ እድሜ 25, 500 ቀናት ገደማ አሉት። ምንም ያህል ዓመት እንኑር ‘ነገ የሚሆነውን አናውቅም። ሕይወታችን ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋሎት ነው።’ (ያዕቆብ 4:13-15) ‘ጊዜና ያልታሰበ አጋጣሚ በሁላችንም ላይ ሊደርስ’ የሚችል በመሆኑ ከአሁን በኋላ ለምን ያህል ጊዜ እንደምንኖር አናውቅም። ስለዚህ መከራዎችን ለመቋቋም፣ ሌሎችን ተገቢ በሆነ መንገድ ለመያዝና አሁኑኑ በይሖዋ አገልግሎት አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ እንችል ዘንድ ጥበብን እንድናገኝ እንጸልይ! (መክብብ 9:11፤ ያዕቆብ 1:5-8) ይሖዋ በቃሉ፣ በመንፈሱና በድርጅቱ አማካኝነት ይመራናል። (ማቴዎስ 24:45-47፤ 1 ቆሮንቶስ 2:10፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17) ጥበበኞች መሆናችን ‘የአምላክን መንግሥት መፈለጋችንን’ እንድንቀጥልና ዕድሜያችንን ለይሖዋ ክብር በሚያመጣና ልቡን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እንድንጠቀምበት ያንቀሳቅሰናል። (ማቴዎስ 6:25-33፤ ምሳሌ 27:11) እርግጥ ነው ይሖዋን በሙሉ ልብ ማምለካችን ሙሉ በሙሉ ከችግር ነፃ ያደርገናል ማለት ባይሆንም ከፍተኛ ደስታ ያስገኝልናል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ