የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አጽናፈ ዓለም የሚተዳደርበትን ሕግ ያወጣው ማን ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ሐምሌ 1
    • 3. የሰማይ አካላት ጠፊ ነገሮች ናቸው ወይስ ዘላለማዊ?

      አርስቶትል በሰማይ አካላትና በምድር መካከል ከፍተኛ ልዩነት እንዳለ ያምን ነበር። እሱ እንደሚለው ከሆነ ምድር የምትለዋወጥ፣ የምትጠፋና እየመነመነች የምትሄድ ሲሆን በከዋክብት የተሞላው ሰማይ የተሠራበት ኢተር ብሎ የጠራው ንጥረ ነገር ግን ለውጥ የማያደርግና ዘላለማዊ ነው። አርስቶትል በሞዴሉ ላይ የገለጻቸው እንደ መስታወት ያሉ ክበቦችና በክበቦቹ ላይ የተጣበቁት የሰማይ አካላት ሊለዋወጡ፣ ሊያረጁ ወይም ከሕልውና ውጪ ሊሆኑ እንደማይችሉ ያምን ነበር።

      መጽሐፍ ቅዱስስ ስለዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላል? መዝሙር 102:25-27 እንዲህ ይላል፦ “አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤ እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ። አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።”

      ከአርስቶትል ዘመን ሁለት ምዕተ ዓመታት ያህል አስቀድሞ የኖረው ይህ መዝሙራዊ ከዋክብት ዘላለማዊ እንደሆኑ፣ ምድር ግን ጠፊ ነገር እንደሆነች በመግለጽ በመካከላቸው ልዩነት እንዳለ አልተናገረም። ከዚህ ይልቅ ሁለቱንም ማለትም ሰማይን እና ምድርን ከይሖዋ አምላክ ጋር አነጻጽሯቸዋል፤ እነዚህን ነገሮች የፈጠረው ኃያል መንፈሳዊ አካል የሆነው ይሖዋ ነው።c ይህ መዝሙር በምድር ላይ የሚገኝ ማንኛውም ነገር ሊጠፋ እንደሚችል ሁሉ ከዋክብትም ጠፊ ነገሮች እንደሆኑ ይጠቁማል። ታዲያ ዘመናዊው ሳይንስ ምን ነገር አረጋግጧል?

      የሥነ ምድር ሳይንስ ምድር ልትጠፋ እንደምትችል ስለሚገልጽ የመጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ የአርስቶትልን ሐሳብ ይደግፋል። እንዲያውም የምድር ዐለቶች አለማቋረጥ በመሸርሸራቸው ሳቢያ መንምነው እየጠፉ ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ በእሳተ ገሞራና በሌሎች ሥነ ምድራዊ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት አዳዲስ ዐለቶች እየተፈጠሩ ነው።

      ይሁንና ስለ ከዋክብትስ ምን ማለት ይቻላል? መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው በተፈጥሯቸው ጠፊ ነገሮች ናቸው? ወይስ አርስቶትል እንዳስተማረው ዘላለማዊ? በ16ኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. የአውሮፓ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች አንድ ኮከብ በአስደናቂ ሁኔታ ሲፈነዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመለከቱ ከዋክብት ዘላለማዊ ናቸው የሚለውን የአርስቶትልን አመለካከት መጠራጠር ጀመሩ። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ሳይንቲስቶች ከዋክብት እንዲህ ባለ ኃይለኛና ቅጽበታዊ ፍንዳታ አማካኝነት ወይም ቀስ በቀስ ተቃጥለው ሌላው ቀርቶ ሟሽሸው እንደሚጠፉ ማስተዋል ችለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች በከዋክብት ፍንዳታ ሳቢያ በተፈጠረ የጋዝ ዳመና ውስጥ አዳዲስ ከዋክብት ሲፈጠሩ ተመልክተዋል። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ የሰማይ አካላትን ከሚያረጅና በሌላ ከሚተካ ልብስ ጋር ማመሳሰሉ ትክክል ነው።d በጥንት ዘመን የኖረው ይህ መዝሙራዊ ከዘመናዊ የሳይንስ ግኝት ጋር የሚስማማ ሐሳብ መጻፍ መቻሉ በጣም የሚያስገርም ነው!

      ያም ሆኖ ‘ታዲያ ምድር ወይም በከዋክብት የተሞላው አጽናፈ ዓለም ሙሉ በሙሉ ከሕልውና ውጪ የሚሆንበት ወይም በሌላ የሚተካበት ጊዜ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ምድርም ሆነ አጽናፈ ዓለም ለዘላለም እንደሚኖሩ ነው። (መዝ 104:5፤ 119:90) እንዲህ ሊሆን የቻለው ግን እነዚህ ፍጥረታት በራሳቸው ዘላለማዊ ስለሆኑ ሳይሆን እነሱን የፈጠረው አምላክ ለዘላለም እንደሚያኖራቸው ቃል ስለገባ ነው። (መዝ 148:4-6) እርግጥ አምላክ ይህን የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ አልተናገረም፤ ይሁንና የሁሉ ነገር ፈጣሪ የሆነው አምላክ አጽናፈ ዓለምን ለዘላለም ለማኖር የሚያስችል ኃይል ይኖረዋል ብሎ ማመን ምክንያታዊ አይሆንም? አንድ በሙያው የተካነ መሐንዲስ ለራሱና ለቤተሰቡ የገነባውን መኖሪያ ቤት በየጊዜው እንደሚያድስ ሁሉ ይሖዋም አጽናፈ ዓለም ለዘላለም እየታደሰ እንዲኖር ማድረግ አያቅተውም።

  • አጽናፈ ዓለም የሚተዳደርበትን ሕግ ያወጣው ማን ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ሐምሌ 1
    • d በ19ኛው መቶ ዘመን የኖረው ዊልያም ቶምሰን (ሎርድ ኬልቪን በመባልም ይታወቃል) የተባለ ሳይንቲስት ማንኛውም ነገር በጊዜ ሂደት እየፈራረሰ የሚሄደው ለምን እንደሆነ የሚገልጸውን ሁለተኛውን የተርሞዳይናሚክስ ሕግ አገኘ። ይህን ሕግ ለማግኘት ከረዱት ነገሮች መካከል አንዱ በመዝሙር 102:25-27 ላይ የሚገኘውን ጥቅስ በጥንቃቄ ማጥናቱ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ