-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2006 | ጥር 1
-
-
የአንባቢያን ጥያቄዎች
መዝሙር 102:26 ምድርና ሰማይ “ይጠፋሉ” ይላል። ይህ ሲባል ፕላኔቷ ምድር ትጠፋለች ማለት ነው?
መዝሙራዊው ለይሖዋ ባቀረበው ጸሎት ላይ እንደሚከተለው ብሏል:- “አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤ እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ።” (መዝሙር 102:25, 26) በጥቅሱ ዙሪያ ያለው ሐሳብ እንደሚያሳየው እነዚህ ቁጥሮች የሚናገሩት ስለ ምድር መጥፋት ሳይሆን ስለ አምላክ ዘላለማዊነት ነው። ከዚህ በተጨማሪ በጥቅሱ ዙሪያ ያለው ሐሳብ ይሖዋ ዘላለማዊ የመሆኑ መሠረታዊ ሐቅ ለአምላክ አገልጋዮች ማጽናኛ የሚሆናቸው ለምን እንደሆነ ይገልጻል።
-
-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2006 | ጥር 1
-
-
ሆኖም ረጅም ዘመን የኖሩት ምድርና ሰማይ እንኳ ከይሖዋ ዘላለማዊነት ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም። ስለሆነም መዝሙራዊው በመቀጠል “እነርሱ [ምድርና ሰማይ] ይጠፋሉ፤ አንት ግን ጸንተህ ትኖራለህ” ብሏል። (መዝሙር 102:26) ግዑዝ የሆኑት ምድርና ሰማይ ሊጠፉ ይችላሉ። እውነት ነው፣ ይሖዋ እነዚህ አካላት ዘላለማዊ እንደሆኑ የተናገረባቸው ቦታዎች አሉ። (መዝሙር 119:90፤ መክብብ 1:4) ሆኖም የአምላክ ዓላማ ቢሆን ኖሮ እነዚህ ነገሮች ሊጠፉ ይችሉ ነበር። በአንጻሩ ግን አምላክ ሊሞት አይችልም። እነዚህ ግዑዝ ፍጥረታት ‘ከዘላለም እስከ ዘላለም ሊጸኑ’ የሚችሉት ይሖዋ ስለሚጠብቃቸው ነው። (መዝሙር 148:6) ይሖዋ እነዚህን ግዑዝ ፍጥረታት በየጊዜው ማደሱን ቢያቆም ኖሮ ‘ሁላቸው እንደ ልብስ ባረጁ’ ነበር። (መዝሙር 102:26) አንድ ሰው ከልብሶቹ ይበልጥ ረጅም ዕድሜ መኖር እንደሚችል ሁሉ ይሖዋም ፍጥረታቱ ሲያልፉ እርሱ መኖሩን ይቀጥላል። ይሁንና በሌሎች ጥቅሶች ላይ እንደምናነበው ይሖዋ ምድርና ሰማይ እንዲያልፉ ፈቃዱ አይደለም። ይሖዋ ግዑዙ ምድርና ሰማይ ለዘላለም እንዲኖሩ መወሰኑን የአምላክ ቃል ያረጋግጥልናል።—መዝሙር 104:5
-