-
ክርስቲያኖች ለአልኮል መጠጥ ምን አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
1. የአልኮል መጠጦችን መጠጣት ስህተት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ የአልኮል መጠጥ መጠጣትን አይከለክልም። እንዲያውም አምላክ ከሰጠን በርካታ ስጦታዎች መካከል “የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ የወይን ጠጅ” እንደሚገኝበት ይገልጻል። (መዝሙር 104:14, 15) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ አንዳንድ ታማኝ ወንዶችና ሴቶች የአልኮል መጠጥ ይጠጡ ነበር።—1 ጢሞቴዎስ 5:23
-
-
ራስህን ለይሖዋ መወሰንና መጠመቅ ያለብህ ለምንድን ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. ይሖዋ ለአንተ ባሳየው ፍቅር ላይ አሰላስል
ይሖዋ ግሩም የሆኑ በርካታ ስጦታዎችን ሰጥቶናል። ታዲያ እኛ በምላሹ ምን ልንሰጠው እንችላለን? ቪዲዮውን ተመልከቱ።
ይሖዋ አንተን እንደሚወድህ ያሳየባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? መዝሙር 104:14, 15ን እንዲሁም 1 ዮሐንስ 4:9, 10ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ ከሰጠህ ስጦታዎች መካከል አንተ በጣም የምታደንቀው የትኛውን ነው?
እነዚህን ስጦታዎች ስታስብ ስለ ይሖዋ ምን ስሜት ያድርብሃል?
አንድ ሰው በጣም የምንወደውን ነገር ስጦታ አድርጎ ሲሰጠን አድናቆታችንን ለእሱ ማሳየት እንፈልጋለን። ዘዳግም 16:17ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ ስላደረገልህ ነገሮች ስታስብ በምላሹ ለእሱ ምን ለመስጠት ትነሳሳለህ?
-