-
የተግሣጽን ዓላማ መረዳትመጠበቂያ ግንብ—2003 | ጥቅምት 1
-
-
መጽሐፍ ቅዱስ ግን ተግሣጽን የሚገልጸው ለየት ባለ መንገድ ነው። ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን “ልጄ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ” ሲል ጽፏል። (ምሳሌ 3:11) ይህ ጥቅስ የሚናገረው በደፈናው ስለ ማንኛውም ተግሣጽ ሳይሆን አምላክ ባወጣቸው የላቁ መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ ስለተመሠረተው ‘የይሖዋ ተግሣጽ’ ነው። መንፈሳዊ ጥቅሞች የሚያስገኘውና ተቀባይነትም የሚኖረው እንዲህ ያለው ተግሣጽ ብቻ ነው። ከዚህ በተቃራኒው ከፍ ካሉት የይሖዋ መሥፈርቶች ጋር በሚቃረን ሰብዓዊ አስተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ተግሣጽ መጥፎና ጎጂ ነው። ከዚህም የተነሳ ብዙዎች ለተግሣጽ አሉታዊ አመለካከት ይይዛሉ።
የይሖዋን ተግሣጽ እንድንቀበል ማሳሰቢያ የሚሰጠን ለምንድን ነው? መለኮታዊ ተግሣጽ አምላክ ለሰብዓዊ ፍጡሮቹ ያለው ፍቅር መግለጫ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። በዚህም ምክንያት ሰሎሞን በመቀጠል እንዲህ ብሏል:- “እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻልና፣ አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ።”—ምሳሌ 3:12
የተግሣጽና የቅጣት ልዩነት ምንድን ነው?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተገለጸው መሠረት ተግሣጽ የተለያዩ ገጽታዎች ያሉት ሲሆን በመመሪያ፣ በትምህርት፣ በሥልጠና፣ በወቀሳና በእርማት አልፎ ተርፎም በቅጣት መልክ ሊሰጥ ይችላል። ይሁን እንጂ በየትኛውም መልክ ቢሆን ይሖዋ ተግሣጽ የሚሠጠው በፍቅር ተገፋፍቶ ሲሆን ዓላማውም ግለሰቡን መጥቀም ነው። ይሖዋ ለማረም ብሎ ተግሣጽ የሚሰጠው ግለሰቡን ለመቅጣት ሲፈልግ ብቻ አይደለም።
-
-
የተግሣጽን ዓላማ መረዳትመጠበቂያ ግንብ—2003 | ጥቅምት 1
-
-
እነዚህ የቅጣት እርምጃዎች “ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ” የሆኑት እንዴት ነው? ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ አምላክ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት “እግዚአብሔርን የማያውቁትን፣ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል” በማለት በእኛ ዘመን የቅጣት እርምጃ እንደሚወስድ ተናግሯል። አክሎም “በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ” ብሏል። (2 ተሰሎንቄ 1:8, 9) በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው እንዲህ ያለው ቅጣት ዓላማ ሰዎቹን ማስተማር ወይም ማስተካከል አይደለም። ይሁን እንጂ ይሖዋ አምላኪዎቹ ተግሣጹን እንዲቀበሉ ሲናገር ንስሐ በማይገቡ ኃጢአተኞች ላይ የሚወስደውን ቅጣት ማመልከቱ አይደለም።
መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋን በዋነኝነት የሚገልጸው ለመቅጣት እንደተዘጋጀ አድርጎ አለመሆኑ ትልቅ ትርጉም ያዘለ ነው። ከዚህ ይልቅ አብዛኛውን ጊዜ የተገለጸው አፍቃሪ አስተማሪና ታጋሽ አሰልጣኝ እንደሆነ ነው። (ኢዮብ 36:22፤ መዝሙር 71:17፤ ኢሳይያስ 54:13) አዎን፣ አንድን ሰው ለማስተካከል ተብሎ የሚሰጥ መለኮታዊ ተግሣጽ ምንጊዜም በፍቅርና በትዕግሥት የተደገፈ ነው። ክርስቲያኖች የተግሣጽን ዓላማ መረዳታቸው ተግሣጽ በመቀበልም ሆነ በመስጠት ረገድ ተገቢ አመለካከት እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል።
-