-
በሥነ ምግባር በረከሰ ዓለም ውስጥ ንጽህናህን ጠብቀህ መኖር ትችላለህመጠበቂያ ግንብ—2000 | ሐምሌ 15
-
-
ሥነ ምግባር የጎደለው ሰው ከሚከተለው መንገድ መራቅ ያስፈለገበት ሌላው ምክንያት ምንድን ነው? ሰሎሞን እንዲህ ሲል መልስ ይሰጣል:- “ክብርህ ለሌላ እንዳትሰጥ፣ ዕድሜህም ለጨካኝ፤ ሌሎች ከሀብትህ እንዳይጠግቡ፣ ድካምህም በባዕድ ሰው ቤት እንዳይሆን። በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፋ ጊዜ ታለቅሳለህ። ”—ምሳሌ 5:9-11
-
-
በሥነ ምግባር በረከሰ ዓለም ውስጥ ንጽህናህን ጠብቀህ መኖር ትችላለህመጠበቂያ ግንብ—2000 | ሐምሌ 15
-
-
‘ዕድሜያችንን፣ ሃብታችንንና የድካማችንን ፍሬ ለሌሎች ወይም ለባዕዳን መስጠትስ’ ምንን ይጨምራል? አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ እንዲህ ይላል:- “የእነዚህ ጥቅሶች ሐሳብ ግልጽ ነው:- ለትዳር ጓደኛ ታማኝ አለመሆን ከፍተኛ ኪሳራ ያስከትል ይሆናል፤ ምክንያቱም በሴትዮዋ ራስ ወዳድነት የሞላበት ፍላጎት ወይም በማኅበረሰቡ ዘንድ በፈጸመው ቅሌት ሳቢያ አንድ ሰው ሲደክምለት የኖረውን ክብር፣ ሥልጣን ወይም ሃብት ሊያጣ ይችላል።” ሥነ ምግባር የጎደለው ግንኙነት ከፍተኛ ኪሳራ ያመጣል!
-