የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ይሖዋ ጥበብን ይሰጣል”
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ኅዳር 15
    • በጥንቷ እስራኤል ይኖር የነበረው ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን የሚከተለውን በፍቅር ላይ የተመሠረተ አባታዊ ቃላት ሰንዝሯል:- “ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ብትቀበል፣ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፣ ጆሮህ ጥበብን እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፣ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ። ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት፣ ለማስተዋልም ድምፅህን ብታነሣ፣ እርስዋንም እንደ ብር ብትፈላልጋት፣ እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፤ የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፣ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ።”​—⁠ምሳሌ 2:​1-5

      ጥበብን በማግኘት ረገድ ኃላፊነቱ የወደቀው በማን ላይ እንደሆነ ትመለከታለህ? በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ‘እንዲህ ብታደርግ’ የሚሉ አባባሎች ሰፍረው እናገኛለን። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ጥበብንም ሆነ ከጥበብ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን ማስተዋልንና እውቀትን ለማግኘት መጣጣር የሚኖርብን እኛው ነን። በመጀመሪያ ግን በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ የሚገኙትን የጥበብ ቃላት ‘ተቀብለን’ በአእምሯችን ውስጥ ‘መሸሸግ’ አለብን። ለዚህም መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ይኖርብናል።

  • “ይሖዋ ጥበብን ይሰጣል”
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ኅዳር 15
    • የምሳሌ መጽሐፍ ሁለተኛ ምዕራፍ “ብትቀበል፣” “ብትይዛት፣” “ብትጠራት፣” “ብትፈላልጋት፣” “ብትሻት” በሚሉ አገላለጾች ምንባቡን ይጀምራል። ጸሐፊው እነዚህን አባባሎች በመድገም ጠበቅ አድርጎ ሊገልጽ የፈለገው ነገር ምንድን ነው? አንድ የማመሳከሪያ መጽሐፍ እንዲህ ይላል:- “እዚህ ላይ ብልሁ ሰው ጥበብን በጥብቅ የመፈለግን አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ ገልጿል።” አዎን፣ ጥበብንና የእርሱ ተዛማጅ ባሕርይ የሆኑትን ማስተዋልንና እውቀትን በትጋት መከታተል ይገባናል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ