-
የአምላክን ቃል የማጥናት ልማድ ይኑርህመጠበቂያ ግንብ—2002 | ታኅሣሥ 1
-
-
9 ሰሎሞን በመቀጠል እንዲህ ብሏል:- “እርስዋንም [እውቀትን] እንደ ብር ብትፈላልጋት፣ እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፤ . . .” (ምሳሌ 2:4) ይህን ስናነብብ ላለፉት ብዙ መቶ ዓመታት ሰዎች የደከሙባቸው እንደ ወርቅና ብር ያሉት የከበሩ ማዕድናት የሚባሉ ነገሮች ትዝ ይሉናል። ሰዎች ለወርቅ ሲሉ እርስ በርስ ተገዳድለዋል። ሌሎች ደግሞ ወርቅ ለማግኘት ሕይወታቸውን በሙሉ ሲማስኑ ኖረዋል። ይሁንና ወርቅ በእርግጥ ዋጋው ምን ያህል ነው? እልም ያለ በረሃ ውስጥ በውሃ ጥም ልትሞት ብትደርስ የትኛውን ማግኘት ትመርጣለህ? አንድ ጥፍጥፍ ወርቅ ወይስ አንድ ብርጭቆ ውኃ? ለወርቅ የሚሰጠው ዋጋ ሰዎች ራሳቸው የተመኑትና በየጊዜው የሚቀያየር ነው።a ያም ሆኖ ሰዎች ወርቅ ለማግኘት በቅንዓት ሲጋደሉ ኖረዋል። ታዲያ እኛ ስለ አምላክና ስለ ፈቃዱ ጥበብ፣ ማስተዋልና እውቀትን ለማግኘት ምንኛ አብልጠን በቅንዓት መጋደል ይኖርብናል! ይሁንና እንዲህ በማድረጋችን የምናገኘው በረከት ምንድን ነው?—መዝሙር 19:7-10፤ ምሳሌ 3:13-18
-
-
የአምላክን ቃል የማጥናት ልማድ ይኑርህመጠበቂያ ግንብ—2002 | ታኅሣሥ 1
-
-
a ከ1979 ወዲህ የወርቅ ዋጋ በእጅጉ የዋዠቀ ሲሆን በ1980 ውስጥ 850 የአሜሪካን ዶላር የነበረው 31 ግራም ወርቅ በ1999 ወደ 252.80 የአሜሪካ ዶላር አሽቆልቁሏል።
-