የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ይሖዋ ጥበብን ይሰጣል”
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ኅዳር 15
    • በጥንቷ እስራኤል ይኖር የነበረው ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን የሚከተለውን በፍቅር ላይ የተመሠረተ አባታዊ ቃላት ሰንዝሯል:- “ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ብትቀበል፣ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፣ ጆሮህ ጥበብን እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፣ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ። ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት፣ ለማስተዋልም ድምፅህን ብታነሣ፣ እርስዋንም እንደ ብር ብትፈላልጋት፣ እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፤ የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፣ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ።”​—⁠ምሳሌ 2:​1-5

  • “ይሖዋ ጥበብን ይሰጣል”
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ኅዳር 15
    • የምሳሌ መጽሐፍ ሁለተኛ ምዕራፍ “ብትቀበል፣” “ብትይዛት፣” “ብትጠራት፣” “ብትፈላልጋት፣” “ብትሻት” በሚሉ አገላለጾች ምንባቡን ይጀምራል። ጸሐፊው እነዚህን አባባሎች በመድገም ጠበቅ አድርጎ ሊገልጽ የፈለገው ነገር ምንድን ነው? አንድ የማመሳከሪያ መጽሐፍ እንዲህ ይላል:- “እዚህ ላይ ብልሁ ሰው ጥበብን በጥብቅ የመፈለግን አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ ገልጿል።” አዎን፣ ጥበብንና የእርሱ ተዛማጅ ባሕርይ የሆኑትን ማስተዋልንና እውቀትን በትጋት መከታተል ይገባናል።

      አስፈላጊውን ጥረት ታደርጋለህን?

      ትጋት የተሞላበት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጥበብን በመፈለግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ሆኖም ይህ ዓይነቱ ጥናት መረጃ ለማግኘት ብቻ ተብሎ ከሚደረገው ንባብ የላቀ መሆን ይኖርበታል። ባነበብነው ነገር ላይ በዓላማ ማሰላሰል ቅዱሳን ጽሑፎችን ለማጥናት የግድ አስፈላጊ የሆነ ክፍል ነው። ጥበብንና ማስተዋልን ማግኘት ማለት ችግሮችን ለመፍታትና ውሳኔ ለማድረግ የተማርናቸውን ነገሮች እንዴት ልንሠራባቸው እንደምንችል ማሰላሰልን ይጠይቃል። እውቀትን መቅሰም፣ ያገኘናቸውን አዳዲስ ትምህርቶች ከዚህ ቀደም ከምናውቃቸው ነገሮች ጋር እንዴት እንደሚስማሙ ቆም ብሎ ማሰብን ይጠይቃል። እንዲህ ያለው ጥልቀት የተሞላበት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጊዜና ብርቱ ጥረት ማድረግን የሚጠይቅ መሆኑን ማን ሊክድ ይችላል? ለዚህ የሚውለው ጊዜና ጉልበት ‘ብርና የተደበቀ ሀብት ለመፈለግ’ ከሚወጣው ጊዜና ጉልበት ጋር የሚመሳሰል ነው። ታዲያ አስፈላጊውን ጥረት ለማድረግ ፈቃደኛ ነህ? ለዚህስ ‘ጊዜ ትዋጃለህ?’​—⁠ኤፌሶን 5:​15, 16

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ