-
ለልብና ለጤንነት የሚበጅ ጥበብንቁ!—2011 | ነሐሴ
-
-
“ሰላም ያለው ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል።”—ምሳሌ 14:30
-
-
ለልብና ለጤንነት የሚበጅ ጥበብንቁ!—2011 | ነሐሴ
-
-
ሰላም ያለው ልብ ያላቸውን ሰዎች እና ቁጣ የሚቀናቸውን ሰዎች በተመለከተ ጆርናል ኦቭ ዚ አሜሪካን ኮሌጅ ኦቭ ካርዲዮሎጂ እንዲህ ይላል፦ ‘በአሁኑ ጊዜ ያሉ የምርምር ውጤቶች እንደሚጠቁሙት ቁጣና ጥላቻ ለልብ ሕመም አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።’ በመሆኑም ይህ መጽሔት እንዲህ ብሏል፦ “የልብ ሕመምን በመከላከልና በማከም ረገድ ውጤታማ ለመሆን . . . ከተለመደው የፊዚዮቴራፒና በመድኃኒቶች አማካኝነት የሚደረግ ሕክምና በተጨማሪ ቁጣንና ጥላቻን በመቆጣጠር ላይ ያተኮረ ሥነ ልቦናዊ ሕክምና ሊያስፈልግ ይችላል።” በቀላል አነጋገር፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ሰላም ያለው ልብ ለጥሩ ጤንነት አስተዋጽኦ ያበረክታል።
-