-
‘ሌሎችን የሚያንጽ መልካም ቃል’ ተናገር‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
-
-
አንደበታችንን መቆጣጠር የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?
4, 5. አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች፣ ቃላት ያላቸውን ኃይል የሚገልጹት እንዴት ነው?
4 አንደበታችንን መቆጣጠር አስፈላጊ የሆነበት አንዱ ትልቅ ምክንያት ቃላት ኃይል ስላላቸው ነው። ምሳሌ 15:4 “ፈውስ የምታመጣ ምላስ የሕይወት ዛፍ ናት፤ አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ትሰብራለች” ይላል።a ውኃ አንድን የጠወለገ ተክል ነፍስ እንደሚዘራበት ሁሉ ፈዋሽ ከሆነ አንደበት የሚወጣ ቃልም የሰሚዎቹን መንፈስ ያድሳል። በአንጻሩ ግን ከጠማማ አንደበት የሚወጣ ክፉ ቃል የሌሎችን መንፈስ ይሰብራል። በእርግጥም የምንናገራቸው ቃላት የመጉዳት ወይም የመፈወስ ኃይል አላቸው።—ምሳሌ 18:21
-