የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ይሖዋ ጥበብን ይሰጣል”
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ኅዳር 15
    • በተጨማሪም እውነተኛ ጥበብና የእርሱ ተዛማጅ የሆኑት ባሕርያት ሥነ ምግባር የጎደላቸው ወንዶችና ሴቶች ከሚከተሉት መጥፎ አካሄድ የሚጠብቁን በመሆናቸው ምንኛ አመስጋኞች ነን! ሰሎሞን ከእነዚህ ባሕርያት የምናገኘውን ጥቅም ሲናገር እንዲህ ብሏል:- “ከጋለሞታ [“ከእንግዳ፣” NW] ሴት አንተን ለመታደግ፣ ቃልዋን ከምታለዝብ ከሌላዪቱም ሴት፤ የሕፃንነት ወዳጅዋን የምትተው የአምላክዋንም ቃል ኪዳን የምትረሳ፤ ቤትዋ ወደ ሞት ያዘነበለ ነው፣ አካሄድዋም ወደ ሙታን ጥላ። ወደ እርስዋ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፣ የሕይወትንም ጎዳና አያገኙም።”​—⁠ምሳሌ 2:​16-19

      ‘ጋለሞታይቱ [“እንግዳዋ፣” NW] ሴት’ በልጅነቷ ያገባችውን ባሏን ሳይሆን አይቀርም “የሕፃንነት ወዳጅዋን” እንደተወች ተደርጋ ተገልጻለች።a (ከሚልክያስ 2:​14 ጋር አወዳድር።) ምንዝር መፈጸም የሚከለክለውን በሕጉ ቃል ኪዳን ውስጥ ተካቶ የሚገኘውን ሕግ ረስታለች። (ዘጸአት 20:​14) መንገዷ ወደ ሞት የሚያደርስ ነው። ከእርሷ ጋር ወዳጅነት የመሠረቱ ሁሉ ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ ተመልሰው ሊወጡ ወደማይችሉበት ቃል በቃል መመለስ ወደማይችሉበት ወደ ሞት አፋፍ ስለሚሄዱ “የሕይወትንም ጎዳና አያገኙም።” ማስተዋልና የማሰብ ችሎታ ያለው ሰው ወደ ፆታ ብልግና የሚመሩ ነገሮችን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሲሆን በዚህ ዓይነቱ ወጥመድ ውስጥ ላለመያዝ በጥበብ ይርቃል።

  • “ይሖዋ ጥበብን ይሰጣል”
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ኅዳር 15
    • [የግርጌ ማስታወሻ]

      a “እንግዳ” [NW] የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከሕጉ ጋር የሚስማማ ነገር ከማድረግ ዘወር በማለታቸው ከይሖዋ የራቁ ሴቶችን ነው። ስለዚህ ጋለሞታይቱ የሌላ አገር ሴት ባትሆንም “እንግዳ” [NW] ተብላ ተጠርታለች።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ