-
የአልኮል መጠጥን በተመለከተ ሚዛናዊ አመለካከት ይኑርህመጠበቂያ ግንብ—2004 | ታኅሣሥ 1
-
-
2. የአልኮል መጠጥን በሚመለከት የትኞቹን ጥያቄዎች እንመረምራለን?
2 አንድ ጥሩ ስጦታ አስደሳች ሊሆን የሚችለው በአግባቡ ጥቅም ላይ ሲውል ብቻ ነው። ለምሳሌ ያህል ማር “መልካም” ነው፤ ሆኖም “ከመጠን በላይ ማር መብላት ጥሩ አይደለም።” (ምሳሌ 24:13፤ 25:27) “ጥቂት የወይን ጠጅ” መጠጣት አስደሳች ሊሆን ቢችልም ከመጠን በላይ መጠጣት ግን ከባድ ችግር ያስከትላል። (1 ጢሞቴዎስ 5:23) መጽሐፍ ቅዱስ “የወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤ በእነዚህ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም” በማለት ያስጠነቅቃል። (ምሳሌ 20:1) ይሁን እንጂ በአልኮል መጠጥ መሳት ሲባል ምን ማለት ነው?a አንድ ሰው ከመጠን በላይ ጠጥቷል የሚባለው ምን ያህል ቢጠጣ ነው? በዚህ ረገድ ሊኖረን የሚገባው ሚዛናዊ አመለካከት ምንድን ነው?
አንድ ሰው በአልኮል መጠጥ ‘የሚስተው’ እንዴት ነው?
3, 4. (ሀ) እስኪሰክሩ ድረስ መጠጣት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተወገዘ መሆኑን የሚያሳየው ምንድን ነው? (ለ) አንዳንድ የስካር ምልክቶች ምንድን ናቸው?
3 በጥንቷ እስራኤል አንድ ልጅ ሆዳምና ሰካራም ሆኖ ከተገኘና ከዚህ አመሉ የማይታረም ከሆነ በድንጋይ ተወግሮ ይገደል ነበር። (ዘዳግም 21:18-21) ሐዋርያው ጳውሎስ “‘ወንድም ነኝ’ እያለ ከሚሴስን ወይም ከሚስገበገብ ወይም ጣዖትን ከሚያመልክ ወይም ከሚሳደብ ወይም ከሚሰክር ወይም ከሚቀማ ጋር እንዳትተባበሩ . . . ከእንደዚህ ዐይነቱ ሰው ጋር ምግብ እንኳ አትብሉ” በማለት ክርስቲያኖችን መክሯል። ከዚህ በግልጽ እንደምናየው እስኪሰክሩ ድረስ መጠጣት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፈጽሞ የተወገዘ ነው።—1 ቆሮንቶስ 5:11፤ 6:9, 10
4 መጽሐፍ ቅዱስ የስካር ምልክቶችን ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ “መልኩ ቀይ ሆኖ፣ በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣ ሰተት ብሎ በሚወርድበትም ጊዜ፣ ወደ ወይን ጠጅ ትክ ብለህ አትመልከት። በመጨረሻው እንደ እባብ ይነድፋል፤ እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል። ዐይኖችህ እንግዳ ነገር ያያሉ፤ አእምሮህም ይቀባዥራል።” (ምሳሌ 23:31-33) አንድ ሰው ከመጠን በላይ ከጠጣ መጠጡ እንደ መርዛማ እባብ በመንደፍ ለሕመም ይዳርገዋል፣ ናላውን ያዞረዋል አልፎ ተርፎም ራሱን እስከመሳት ያደርሰዋል። የሰከረ ሰው ‘እንግዳ ነገር ሊያይ’ ማለትም በቁሙ ሊቃዥ ይችላል። እንዲሁም ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንደሚባለው ሌላ ጊዜ መናገር የማይፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ መናገር ወይም መቀባዠር ይጀምራል።
5. የአልኮል መጠጥን አዘውትሮ የመውሰድ ልማድ ጎጂ የሚሆነው እንዴት ነው?
5 አንድ ሰው የስካር ምልክት እንዳይታይበት እየተጠነቀቀ የመጠጣት ልማድ ቢኖረውስ? አንዳንዶች ብዙ ጠጥተውም እንኳ የስካር ምልክት ላይታይባቸው ይችላል። ይሁን እንጂ እንዲህ ያለው ልማድ ራስን ማሞኘት ነው። (ኤርምያስ 17:9) አንድ ሰው እንዲህ ያለ ልማድ ካለው ይዋል ይደር እንጂ የአልኮል ጥገኛና ‘ሱሰኛ’ መሆኑ አይቀርም። (ቲቶ 2:3) ካሮላይን ናፕ የተባሉ ጸሐፊ የአልኮል ሱሰኛ ወደመሆን የሚያደርሰውን ሒደት በተመለከተ ሲናገሩ “አንድ ሰው የአልኮል ሱሰኛ የሚሆነው ቀስ በቀስና ምንም ሳይታወቀው ነው” ብለዋል። በእርግጥም የአልኮል መጠጥ አደገኛ ወጥመድ ሊሆን ይችላል!
6. አንድ ሰው ብዙ የመጠጣትና የመብላት ልማድ እንዳይጠናወተው መጠንቀቅ ያለበት ለምንድን ነው?
6 በተጨማሪም ኢየሱስ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ። አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይመጣባችኋል። ምክንያቱም ያ ቀን በምድር ላይ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ በድንገት ያጠምዳቸዋል” ሲል የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ልብ በል። (ሉቃስ 21:34, 35 የ1980 ትርጉም) አንድ ሰው ባይሰክርም እንኳ የአልኮል መጠጥ በመጠጣቱ ምክንያት በአካላዊም ሆነ በመንፈሳዊ ሊደብተውና ሊጫጫነው ይችላል። እንዲህ ባለ ሁኔታ ላይ እያለ የይሖዋ ቀን ቢደርስበትስ?
-
-
የአልኮል መጠጥን በተመለከተ ሚዛናዊ አመለካከት ይኑርህመጠበቂያ ግንብ—2004 | ታኅሣሥ 1
-
-
10. የአልኮል መጠጥ በአእምሮ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችለው እንዴት ነው? ይህስ አደገኛ የሆነው ለምንድን ነው?
10 ከመጠን በላይ መጠጣት አካላዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም ጉዳት አለው። መጽሐፍ ቅዱስ “የወይን ጠጅ ስካርም አእምሮን ያጠፋል” በማለት ይናገራል። (ሆሴዕ 4:11 የ1954 ትርጉም) የአልኮል መጠጥ በአእምሮ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። የአሜሪካ ብሔራዊ የአደገኛ ዕፅ መቆጣጠሪያ ተቋም የሚያሳትመው ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦ “አንድ ሰው የአልኮል መጠጥ ሲጠጣ ወደ ሰውነቱ ገብቶ በደም ሥሩ አማካኝነት ቶሎ አናቱ ላይ ይወጣል። ከዚያም አስተሳሰብንና ስሜትን የሚቆጣጠረውን የአእምሮ ክፍል ያፈዝዘዋል። በዚህ ጊዜ ግለሰቡ ራሱን መቆጣጠር ይሳነዋል።” እዚህ ደረጃ ላይ ከደረስን ‘ልንስት፣’ የማይፈለጉ ነገሮችን ለማድረግ ድፍረት ልናገኝና ራሳችንን ለብዙ ፈተና ልናጋልጥ እንችላለን።—ምሳሌ 20:1
-