የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሰዎች የምትሰጠውን ምክር ይቀበሉታል?
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ጥር 15
    • ምክር በሚሰጥበት ጊዜ ትክክለኛ ቃላትን መምረጥ በጣም አስፈላጊ ነው። ጠቢቡ ሰሎሞን “የወርቅ እንኮይ በብር ፃሕል ላይ፤ የጊዜው ቃል እንዲሁ ነው” በማለት ተናግሯል። (ምሳሌ 25:​11) ምናልባት ይህን የተናገረው ከወርቅ ተቀርጾ የተሠራ ፖም የተቀመጠበትን ውብ የብር ሳህን በአእምሮው ይዞ ሊሆን ይችላል። ይህ ለዓይን ምንኛ ማራኪ ነው! በስጦታ መልክ ቢሰጥህ እንዴት ባለ አድናቆት ትቀበል ነበር! በተመሳሳይም በጥንቃቄ የተመረጡና በጸጋ የተሞሉ ቃላት ልትረዳው የምትሞክረውን ግለሰብ በጥሩ ሁኔታ ሊማርኩ ይችላሉ።​—⁠መክብብ 12:​9, 10

  • ሰዎች የምትሰጠውን ምክር ይቀበሉታል?
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ጥር 15
    • ሰሎሞን እንደተናገረው የምክር ቃል ‘በተገቢው ጊዜ መነገር’ ይኖርበታል። ምክር የታለመለትን ዓላማ እንዲያከናውን ከተፈለገ ምክር የሚሰጥበትን ጊዜ በጥንቃቄ መምረጡ በጣም አስፈላጊ ነው! የመብላት ፍላጎት ለሌለው ሰው ምግብ ማቅረብ ምንም ጥቅም እንደ ሌለው የታወቀ ነው። ምናልባት በቅርቡ ጥግብ ብሎ በልቶ አሊያም አሞት ሊሆን ይችላል። አንድ ሰው መብላት ሳይፈልግ አስገድዶ እንዲመገብ ማድረግ ጥበብ አይደለም፤ ተቀባይነትም የለውም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ