የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋን መታመኛችሁ አድርጉት
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | መስከረም 1
    • 18, 19. መጽሐፍ ቅዱስ በይሖዋ እንድንታመን የሚያበረታታን እንዴት ነው? ሆኖም አንዳንዶች በዚህ ረገድ ምን የተሳሳተ አመለካከት አላቸው?

      18 የአምላክ ቃል እንዲህ ሲል ያሳስበናል:- “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።” (ምሳሌ 3:5, 6) እነዚህ የሚያበረታቱና አስደሳች ቃላት ናቸው። በእርግጥም በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ የምንወደውን አባታችንን ያህል እምነት ሊጣልበት የሚችል ሌላ ማንም የለም። ያም ሆኖ በምሳሌ መጽሐፍ ውስጥ የሰፈሩትን እነዚህን ቃላት ተግባራዊ ማድረግ የማንበቡን ያህል ቀላል አይደለም።

  • ይሖዋን መታመኛችሁ አድርጉት
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | መስከረም 1
    • 22, 23. (ሀ) ችግሮች ሲያጋጥሙን በይሖዋ መታመን የሚኖርብን ለምንድን ነው? እንዲህ ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው? (ለ) በሚቀጥለው ርዕስ ላይ የሚብራራው ምንድን ነው?

      22 ይሁንና ምሳሌ 3:​6 እንደሚያሳየው ‘በመንገዳችን ሁሉ ይሖዋን ማወቅ ያለብን’ ችግሮች ሲያጋጥሙን ብቻ አይደለም። በዕለታዊ ሕይወታችን የምናደርጋቸው ውሳኔዎች በይሖዋ እንደምንታመን የሚያሳዩ መሆን አለባቸው። ችግሮች በሚከሰቱበት ጊዜ ተስፋ መቁረጥ፣ መደናገጥ ወይም ሁኔታውን ከሁሉ በተሻለ መንገድ መወጣት እንድንችል ይሖዋ የሚሰጠንን መመሪያ ገሸሽ ማድረግ የለብንም። ፈተናዎች ሲያጋጥሙን የይሖዋን ሉዓላዊነት ለመደገፍ፣ የሰይጣንን ውሸታምነት ለማጋለጥ እንዲሁም ታዛዥነትንና ይሖዋ የሚደሰትባቸውን ሌሎች ባሕርያት ለማዳበር እንደሚያስችሉ አጋጣሚዎች አድርገን ልናያቸው ይገባል።​—⁠ዕብራውያን 5:7, 8

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ