የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ወዳጅነት አጎልብቱ
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ጥር 15
    • ጠቢቡ ንጉሥ በመቀጠል እንዲህ ይላል:- “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።”​—⁠ምሳሌ 3:​5, 6

  • ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ወዳጅነት አጎልብቱ
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ጥር 15
    • ‘በመንገዳችን ሁሉ ይሖዋን ማወቅ’ የምንችለው እንዴት ነው? መዝሙራዊው በመንፈስ ተገፋፍቶ እንዲህ በማለት ተናግሯል:- “ስላደረግኸው ነገር ሁሉ አስባለሁ፤ ስለ ታላላቅ ሥራዎችህም በማሰላሰል አስታውሳለሁ።” (መዝሙር 77:​12) አምላክ በዓይን የማይታይ በመሆኑ በታላላቅ ሥራዎቹና ሕዝቦቹን ስለያዘበት መንገድ ማሰላሰሉ ከእርሱ ጋር የመሠረትነውን የጠበቀ ወዳጅነት ለማጠንከር ከፍተኛ እገዛ ያደርግልናል።

      በተጨማሪም ጸሎት ይሖዋን ለማየት የሚያስችል አንዱ አስፈላጊ መንገድ ነው። ንጉሥ ዳዊት “ቀኑን ሁሉ” ያለማቋረጥ ይሖዋን ይጠራ ነበር። (መዝሙር 86:​3) ዳዊት በበረሃ ስደት ላይ እያለ ሌሊቱን በሙሉ ሲጸልይ ያድር ነበር። (መዝሙር 63:​6, 7) ሐዋርያው ጳውሎስ “ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ” በማለት አጥብቆ አሳስቧል። (ኤፌሶን 6:​18) ምን ያህል አዘውትረን እንጸልያለን? ከአምላክ ጋር በግል ልባዊ የሐሳብ ግንኙነት መመሥረት ያስደስተናል? ችግር በሚያጋጥመን ጊዜ እንዲረዳን እንማጸነዋለን? አንድ አስፈላጊ የሆነ ውሳኔ ከማድረጋችን በፊት አመራር ለማግኘት በጸሎት እንጠይቀዋለን? ለይሖዋ የምናቀርበው ከልብ የመነጨ ጸሎት በእርሱ ዘንድ ተወዳጅ ያደርገናል። እንዲሁም ለእርሱ የምናቀርበውን ጸሎት እንደሚሰማና ‘መንገዳችንን የተቃና እንደሚያደርግልን’ ማረጋገጫ አለን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ