የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለዘመናዊው ኑሮ ተግባራዊ ጥቅም የሚሰጥ መጽሐፍ
    ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ
    • ብዙ ጊዜ የአንድ ሰው አእምሮአዊና ስሜታዊ ጤና በአካላዊ ጤንነቱ ላይ የሚያስከትለው ውጤት ይኖራል። ለምሳሌ ያህል ቁጣ ጉዳት እንደሚያስከትል በሳይንሳዊ ጥናቶች ተረጋግጧል። በዱክ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ማዕከል የሥነ ባሕርይ ምርምር ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሬድፎርድ ዊልያምስና ባለቤታቸው ቨርጅንያ ዊልያምስ አንገር ኪልስ በተባለው መጽሐፋቸው እንዲህ ብለዋል:- “እስካሁን ከተገኙት ማስረጃዎች አብዛኞቹ ግልፍተኛ ሰዎች ብዙ ወዳጆች ስለማይኖሩአቸው፣ በሚቆጡበት ጊዜ ሕዋሶቻቸው ከልክ በላይ ስለሚሠሩ፣ ቁጣቸውን ለማብረድ ከመጠን በላይ ስለሚበሉ ወይም ደግሞ ስለሚጠጡ ወይም ስለሚያጨሱና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች የተነሣ በልብ በሽታና (በሌሎች በሽታዎች) የመያዛቸው ዕድል በጣም ከፍተኛ ነው።”13

      እነዚህን የመሰሉ ሳይንሳዊ ጥናቶች ከመደረጋቸው በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታት በፊት መጽሐፍ ቅዱስ ቀላልና ግልጽ በሆነ አነጋገር በአካላዊ ጤንነትና በስሜት መካከል ዝምድና መኖሩን አመልክቷል። “ትሑት ልብ የሥጋ ሕይወት ነው፣ ቅንዓት ግን አጥንትን ያነቅዛል።” (ምሳሌ 14:​30፤ 17:​22) መጽሐፍ ቅዱስ “አትቆጣ፣ አትናደድም” በተጨማሪም “ለቁጣ ችኩል አትሁን” በማለት የጥበብ ምክር ይሰጣል።​—⁠መዝሙር 37:​8 የ1980 ትርጉም፤ መክብብ 7:​9

  • ለዘመናዊው ኑሮ ተግባራዊ ጥቅም የሚሰጥ መጽሐፍ
    ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ
    • “ቅሬታህን ለመግለጽ አትቸኩል፣ ቅሬታቸውን የሚያስታምሙ ሞኞች ናቸውና።” (መክብብ 7:​9፤ ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብል) አብዛኛውን ጊዜ የስሜት ግንፋሎት ከድርጊት ይቀድማል። ለመቆጣት የሚቸኩል ወይም ግልፍተኛ የሆነ ሰው ይህ ጠባዩ በኋላ የሚጸጸትበት ነገር እንዲያደርግ ወይም እንዲናገር ስለሚያደርገው ሞኝ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ