-
ደስተኛ ለመሆን የሚያስችል አስተማማኝ መመሪያመጠበቂያ ግንብ—2006 | ሰኔ 15
-
-
መክብብ 9:5, 10 እንዲህ ይላል:- “ሙታን ግን ምንም አያውቁምና፤ . . . ልትሄድበት ባለው መቃብር [“ሲኦል፣” የግርጌ ማስታወሻ] ውስጥ መሥራትም ሆነ ማቀድ፣ ዕውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።” ሲኦል ምንድን ነው? ሰዎች ሲሞቱ የሚሄዱበት የሰው ልጆች መቃብር ነው። በመቃብር ውስጥ የሚገኙ ሙታን በድን ናቸው፤ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አያደርጉም፣ የሚሰማቸው ወይም የሚያስቡት ነገር የለም። ሙታን ኃይለኛ እንቅልፍ የወሰዳቸው ያህል ነው።a ስለዚህ አምላክ የምንወዳቸውን ሰዎች በሞት በመንጠቅ በሰማይ ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ እንደማይወስዳቸው መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያሳያል። ሰዎች ሲሞቱ ከሕልውና ውጭ ሆነው ወደ መቃብር ይወርዳሉ።
-
-
ደስተኛ ለመሆን የሚያስችል አስተማማኝ መመሪያመጠበቂያ ግንብ—2006 | ሰኔ 15
-
-
a ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ (2003) ሲኦልን “ሕመምም ሆነ ደስታ፣ ቅጣትም ሆነ ሽልማት የሌለበት ቦታ” እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል።
-