የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በአምላክ ፊት ያለባችሁን ሁለንተናዊ ግዴታ እየፈጸማችሁ ነውን?
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ኅዳር 15
    • 12. በመክብብ 12:​11, 12 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን የሰሎሞን አነጋገር በራስህ አባባል እንዴት ብለህ ትገልጸዋለህ?

      12 ምንም እንኳ ዘመናዊ የማተሚያ ዘዴዎች ያልነበሩ ቢሆንም በሰሎሞን ዘመን በጣም ብዛት ያላቸው መጻሕፍት ነበሩ። እንዲህ ዓይነቱ ሥነ ጽሑፍ እንዴት መታየት ነበረበት? ሰሎሞን እንዲህ ይላል:- “የጠቢባን ቃል እንደ በሬ መውጊያ ነው፣ የተሰበሰቡትም ከአንድ እረኛ የተሰጡት ቃላት እንደ ተቸነከሩ ችንካሮች ናቸው። ከዚህም ሁሉ በላይ፣ ልጄ ሆይ፣ ተግሣጽን ስማ፤ ብዙ መጻሕፍትን ማድረግ ፍጻሜ የለውም፣ እጅግም ምርምር ሰውነትን ያደክማል።”​—⁠መክብብ 12:​11, 12

  • በአምላክ ፊት ያለባችሁን ሁለንተናዊ ግዴታ እየፈጸማችሁ ነውን?
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ኅዳር 15
    • 14. (ሀ) ‘ብዙ ትኩረት’ መስጠት የማያስፈልገው ለምን ዓይነት መጻሕፍት ነው? (ለ) ይበልጥ ትኩረት መስጠት የሚኖርብን ለየትኛው ዓይነት ጽሑፍ ነው? ለምንስ?

      14 ታዲያ ሰሎሞን መጻሕፍትን በተመለከተ እንዲህ ዓይነት አስተያየት የሰጠው ለምንድን ነው? ይህ ዓለም የሚያቀርባቸው ማለቂያ የሌላቸው መጻሕፍት ከይሖዋ ቃል ጋር ሲነጻጸሩ በሰብዓዊ አመለካከት የተሞሉ ናቸው። ይህ ሰብዓዊ አስተሳሰብ ደግሞ በአብዛኛው የሰይጣንን አመለካከት የሚያንጸባርቅ ነው። (2 ቆሮንቶስ 4:​4) ስለዚህ እንዲህ ያሉትን መጻሕፍት ‘እጅግ መመርመር’ ምንም ዓይነት ዘላቂ ጥቅም አያስገኝም። እንዲያውም እንዲህ ያሉ መጻሕፍትን ማብዛት መንፈሳዊ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ልክ እንደ ሰሎሞን የአምላክ ቃል ስለ ሕይወት በሚናገረው ነገር ላይ እናሰላስል። እንዲህ ማድረጋችን እምነታችንን ያጠነክርልናል፤ ወደ ይሖዋም ይበልጥ ያቀርበናል። ለሌሎች መጻሕፍት ወይም የመመሪያ ምንጮች ከመጠን ያለፈ ትኩረት መስጠት ሊያደክመን ይችላል። በተለይ እነዚህ በሰብዓዊ ጥበብ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎች ከአምላካዊ ጥበብ ጋር የሚጋጩ ከሆኑ መጥፎ ከመሆናቸውም በላይ በአምላክና በዓላማዎቹ ላይ ያለንን እምነት ያጠፉብናል። ስለሆነም በሰሎሞን ዘመንም ሆነ በእኛ ዘመን የላቀ ጥቅም ያላቸው መጻሕፍት ‘የአንዱን እረኛ’ ማለትም የይሖዋ አምላክን ጥበብ የሚያንጸባርቁ መጻሕፍት መሆናቸውን እናስታውስ። 66 የቅዱሳን ጽሑፎች መጻሕፍትን ሰጥቶናል፤ ትልቅ ትኩረት መስጠት የሚኖርብን ለእነዚህ መጻሕፍት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁም ‘ታማኙ ባሪያ’ የሚያዘጋጃቸው ጠቃሚ የሆኑ ጽሑፎች ‘የአምላክን እውቀት’ እንድናገኝ ያስችሉናል።​—⁠ምሳሌ 2:​1-6

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ