-
የማሕልየ መሓልይ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦችመጠበቂያ ግንብ—2006 | ኅዳር 15
-
-
1:2, 3 የ1954 ትርጉም—የእረኛው ፍቅር ትውስታ እንደ ወይን ጠጅ፣ ስሙም እንደሚፈስ ዘይት ተደርጎ የተገለጸው ለምንድን ነው? የወይን ጠጅ የሰውን ልብ ደስ እንደሚያሰኝና ዘይትም ራስ ላይ ሲፈስ እንደሚያረካ ሁሉ ልጃገረዷም የእረኛውን ስምና ፍቅሩን ስታስታውስ ትበረታታለች እንዲሁም ትጽናናለች። (መዝሙር 23:5፤ 104:15) በተመሳሳይም እውነተኛ ክርስቲያኖች በተለይ ደግሞ ቅቡዓኑ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳያቸውን ፍቅር በማሰብ ማበረታቻና ማጽናኛ ያገኛሉ።
-