-
ለዘመናችን የሚሆን መልእክት ያስተላለፈ ጥንታዊ ነቢይየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
ሥርዓት አልበኝነት በነገሠበት ዘመን የኖረ ጻድቅ ሰው
4. ኢሳይያስ ማን ነበር? የይሖዋ ነቢይ ሆኖ ያገለገለውስ መቼ ነበር?
4 ኢሳይያስ “የአሞጽ ልጅ ”a መሆኑን በመጽሐፉ የመጀመሪያ ቁጥር ላይ ካስተዋወቀ በኋላ “በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ” የአምላክ ነቢይ ሆኖ እንዳገለገለ ይነግረናል። (ኢሳይያስ 1:1) በዚህ መሠረት ኢሳይያስ ከ46 ለማያንሱ ዓመታት በይሁዳ ብሔር መካከል የአምላክ ነቢይ ሆኖ አገልግሏል። እንደዚያ ከሆነ አገልግሎቱን የጀመረው በንጉሥ ዖዝያን የግዛት ዘመን ማብቂያ ላይ ማለትም በ778 ከዘአበ ገደማ መሆን አለበት።
-
-
ለዘመናችን የሚሆን መልእክት ያስተላለፈ ጥንታዊ ነቢይየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
a የኢሳይያስ አባት የሆነው አሞጽና በዖዝያን የግዛት ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ትንቢት ይናገር የነበረው እንዲሁም በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነውን መጽሐፍ በስሙ የጻፈው አሞጽ ሊምታቱብን አይገባም።
-