የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ተመልሶ የተቋቋመ ገነት!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 20. በመጀመሪያው መቶ ዘመን እዘአ ብቅ ያለው አዲስ እስራኤል የትኛው ነው?

      20 ይሖዋ የወሰነው ጊዜ ሲደርስ ሌላ እስራኤል ማለትም መንፈሳዊ እስራኤል ወደ ሕልውና መጥቷል። (ገላትያ 6:​16) ኢየሱስ በምድር ባከናወነው አገልግሎት ወቅት ለዚህ አዲስ እስራኤል መወለድ ሁኔታውን አመቻችቷል። ንጹሕ አምልኮን መልሶ ያቋቋመ ሲሆን በትምህርቶቹ አማካኝነትም የእውነት ውኃ እንደገና መፍሰስ ጀምሯል። በአካላዊም ሆነ በመንፈሳዊ የታመሙትን ፈውሷል። የአምላክ መንግሥት ምሥራች ሲታወጅም የደስታ ዝማሬ ተሰምቷል። ሞቶ ትንሣኤ ካገኘ በኋላ ሰባት ሳምንታት ያህል ቆይቶ ክብር የተቀዳጀው ኢየሱስ የክርስቲያን ጉባኤን ማለትም በፈሰሰው የኢየሱስ ደም ተዋጅተው የአምላክ መንፈሳዊ ልጆችና የኢየሱስ ወንድሞች በመሆን በመንፈስ ቅዱስ ከተቀቡ አይሁዶችና ሌሎች ሰዎች የተውጣጣውን መንፈሳዊ እስራኤል አቋቁሟል።​—⁠ሥራ 2:​1-4፤ ሮሜ 8:​16, 17፤ 1 ጴጥሮስ 1:​18, 19

      21. በመጀመሪያው መቶ ዘመን ከነበረው የክርስቲያን ጉባኤ ጋር በተያያዘ መንገድ የኢሳይያስ ትንቢት ፍጻሜ ናቸው ሊባሉ የሚችሉት ክንውኖች የትኞቹ ናቸው?

      21 ሐዋርያው ጳውሎስ የመንፈሳዊ እስራኤል አባላት ለሆኑት ሰዎች ሲጽፍ የ⁠ኢሳይያስ 35:​3ን ቃላት በመጥቀስ “የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጒልበቶች አቅኑ” ብሏል። (ዕብራውያን 12:​12) እንግዲያው በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው የ⁠ኢሳይያስ ምዕራፍ 35 ቃላት በመጀመሪያው መቶ ዘመንም ተፈጻሚነት ነበራቸው። ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ተዓምራዊ በሆነ መንገድ የዕውራን ዓይን እንዲያይ የደንቆሮዎች ጆሮ እንዲሰማ አድርገዋል። ‘አንካሶች’ በእግራቸው እንዲሄዱና መናገር የተሳናቸው እንዲናገሩ አድርገዋል። (ማቴዎስ 9:​32፤ 11:​5፤ ሉቃስ 10:​9) ከዚህ ይበልጥ ትርጉም ያለው ግን ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ከሐሰት ሃይማኖት ነፃ ወጥተው በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ በመንፈሳዊ ገነት መካከል ለመገኘት መብቃታቸው ነው። (ኢሳይያስ 52:​11፤ 2 ቆሮንቶስ 6:​17) ከባቢሎን እንደተመለሱት አይሁዳውያን ሁሉ ከሐሰት ሃይማኖት ያመለጡት እነዚህ ሰዎችም አዎንታዊ አመለካከትና የድፍረት መንፈስ ማሳየታቸው አስፈላጊ ነበር።​—⁠ሮሜ 12:​11

  • ተመልሶ የተቋቋመ ገነት!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 23, 24. ከ1919 ጀምሮ የኢሳይያስ ቃላት በአምላክ ሕዝብ መካከል ፍጻሜያቸውን ያገኙት በምን መንገዶች ነው?

      23 ይሁን እንጂ በ1919 ሁኔታዎች ተለወጡ። ይሖዋ ሕዝቡን ከምርኮ ነፃ አወጣቸው። ቀደም ሲል አምልኳቸውን በክለውባቸው የነበሩትን የሐሰት ትምህርቶች ማስወገድ ጀመሩ። ከዚህ የተነሳ ፈውስ አገኙ። ዛሬም ጭምር በምድር ዙሪያ እየተስፋፋ ባለው መንፈሳዊ ገነት ውስጥ ለመገኘት በቅተዋል። ለአምላክ ቅዱስ መንፈስ አሠራር ንቁ በመሆንና ዘወትር ወደ ይሖዋ ተጠግቶ መኖር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በመገንዘብ በመንፈሳዊ ሁኔታ ዕውራን የነበሩት ማየት ችለዋል እንዲሁም ደንቆሮ የነበሩት መስማት ችለዋል። (1 ተሰሎንቄ 5:​6 NW፤ 2 ጢሞቴዎስ 4:​5 NW) አፋቸው የተፈታው ክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለሌሎች በማወጅ ‘ዝማሬያቸውን’ ለማሰማት ይጓጓሉ። (ሮሜ 1:​15 የ1980 ትርጉም) በመንፈሳዊ ደካማ ወይም “አንካሳ” የነበሩት ሰዎች አሁን ቀናተኞችና ደስተኞች ሆነዋል። በምሳሌያዊ አነጋገር ‘እንደ ሚዳቋ ይዘልላሉ።’

  • ተመልሶ የተቋቋመ ገነት!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 25. ኢሳይያስ ምዕራፍ 35 ቃል በቃል ፍጻሜውን የሚያገኝበት መንገድ ይኖር ይሆን? አብራራ።

      25 ስለ ወደፊቱስ ጊዜ ምን ለማለት ይቻላል? የኢሳይያስ ትንቢት ቃል በቃል ፍጻሜውን የሚያገኝበት መንገድ ይኖር ይሆን? አዎን። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ኢየሱስና ሐዋርያቱ ያከናወኗቸው ተዓምራዊ ፈውሶች ይሖዋ ወደፊት እንዲህ ያሉ ፈውሶችን በሰፊው ለማከናወን ፍላጎቱም ሆነ አቅሙ እንዳለው አመልክተዋል። በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈው መዝሙር በምድር ላይ ሰላማዊ ሁኔታ ስለሚሰፍንበት ዘላለማዊ ሕይወት ይናገራል። (መዝሙር 37:​9, 11, 29) ኢየሱስ ሰዎች በገነት ውስጥ እንደሚኖሩ ቃል ገብቷል። (ሉቃስ 23:​43) ቃል በቃል ስለምትቋቋመው ገነት የሚገልጸው ተስፋ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ተጠቅሶ እናገኘዋለን። በዚያ ወቅት ዓይነ ስውራን፣ ደንቆሮዎች፣ አንካሶችና መናገር የተሳናቸው ሰዎች ቃል በቃል ዘላቂ ፈውስ ያገኛሉ። ሐዘንና ትካዜ ከሰዎች ፊት ይሸሻሉ። ለዘላለም ዓለም ደስታና ሐሴት ይሰፍናል።​—⁠ራእይ 7:​9, 16, 17፤ 21:​3, 4

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ