የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “እጅግ ብዙ ሰዎች” ወደ አምላክ ድርጅት የሚወስደውን “ጐዳና” ያዙ
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 5 ይህም በሚከተሉት የኢሳይያስ 35 ቃላት ውስጥ ተተንብዮአል:- “በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ይገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል። በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል፣ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረበዳ ውኃ፣ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና። ደረቂቱ ምድር ኩሬ፣ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች፤ ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ልምላሜና ሸምበቆ ደንገልም ይሆንበታል።”— ኢሳይያስ 35:5–7

  • “እጅግ ብዙ ሰዎች” ወደ አምላክ ድርጅት የሚወስደውን “ጐዳና” ያዙ
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 7. የቀሪዎቹ የማስተዋል ዓይኖች ከ1914 በፊት በፍጹም ያላዩት ነገር ምን ነበር? ይሁን እንጂ ‘ዕውር’ ዓይኖቻቸው ተከፈቱላቸውን?

      7 ከአሕዛብ ዘመን ፍጻሜ በፊት የመንፈሳዊ እስራኤላውያን የመረዳት ዓይኖች በ1914 የሚፈነዳው የዓለም ችግር አብቅቶ ከእነርሱ መካከል ቀሪዎቹ ገና በሕይወት እንደሚቆዩ ለማየት በፍጹም አልተከፈቱም ነበር። ከዚህም ሌላ እነርሱና የ“ሌሎች በጐች” ክፍል የሆኑ “እጅግ ብዙ ሰዎች” ስለ አምላክ መሲሐዊ መንግሥት መቋቋም ዓለም አቀፍ ምስክርነት የመስጠት መብት በማግኘት እንደሚባረኩ አልተረዱም ነበር። ስለዚህ በመንፈሳዊ ዕውር የነበሩት የቀሪዎቹ ዓይኖች በ1919 እንዲከፈቱ ተደረጉ፤ እነዚህ የተከፈቱ ዓይኖች ከፊታቸው ያለውን ጊዜ ሲመለከቱ እንዴት ያለ ግሩም ተስፋ ታያቸው!

      8. በሴዳር ፖይንት ኦሀዮ የተደረጉት ሁለት ትልልቅ ስብሰባዎች እንደገና በተደራጁት ቀሪዎች መንፈሳዊ ጆሮዎችና ምላሶች ላይ ምን ውጤት ነበራቸው?

      8 በ1919 እና በ1922 በሴዳር ፖይንት ኦሀዮ ባደረጓቸው ስብሰባዎቻቸው ላይ በፊታቸው ስለተዘረጋው ሥራ ተነገራቸው። በፊታቸው ላለው ሥራ ተዘጋጁ። መንፈሳዊ ጆሮቻቸውም የሚነሽጠውን የአምላክን መንግሥት መልእክት ለመስማትና እርሱን የማወጁን አስፈላጊነት ለመረዳት ተከፍተው ነበር። ለረጅም ጊዜ ሲጸልዩለት ለነበረው መንግሥት እንደ ምስክሮች ሆነው ለማገልገል በተገቢ መንገድ ልክ እንደሚዳቋ ዘልለው ነበር። እስከዚህን ጊዜ ድረስ ዲዳ የነበረው ምላሳቸውም በሰማይ ላይ ሥልጣን ስለያዘው ስለ ሰማያዊው መሲሐዊ መንግሥት በደስታ መጮኽ ጀመረ።— ራእይ 14:1–6

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ