የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ንጉሡ ያሳየው እምነት ተካሰ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 28. ሕዝቅያስ በተዓምራዊ መንገድ ከተፈወሰ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያደረገው የተሳሳተ ውሳኔ ምን ነበር?

      28 ሕዝቅያስ የታመነ ቢሆንም ፍጹም አልነበረም። ይሖዋ ከሕመሙ ከፈወሰው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ባደረገው ውሳኔ ከባድ ስህተት ሠርቷል። ኢሳይያስ ሁኔታውን እንዲህ ሲል ይገልጻል:- “በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት። ሕዝቅያስም ደስ አለው፣ ግምጃ ቤቱንም፣ ብሩንና ወርቁንም፣ ቅመሙንና የከበረውንም ዘይት፣ መሣርያም ያለበትን ቤት ሁሉ፣ በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።”​—⁠ኢሳይያስ 39:​1, 2b

      29. (ሀ) ሕዝቅያስ ሀብቱን ለባቢሎን ልዑክ ሲያስጎበኝ ምን አስቦ ሊሆን ይችላል? (ለ) የሕዝቅያስ የተሳሳተ ውሳኔ የሚያስከትለው መዘዝ ምን ይሆናል?

      29 አሦር በይሖዋ መልአክ ከፍተኛ ሽንፈት ከገጠመው በኋላም ቢሆን ባቢሎንን ጨምሮ ብዙ ብሔራትን ያስፈራራ ነበር። ሕዝቅያስ የወደፊት አጋር ሊሆነኝ ይችላል ብሎ በማሰብ የባቢሎንን ንጉሥ ለማስደመም ፈልጎ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ይሖዋ የሚፈልገው የይሁዳ ነዋሪዎች ከጠላቶቻቸው ጋር ግንባር እንዲፈጥሩ ሳይሆን በእርሱ እንዲታመኑ ነው! በነቢዩ ኢሳይያስ አማካኝነት ይሖዋ የሕዝቅያስን የወደፊት ዕጣ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል:- “እነሆ፣ በቤትህ ያለው ሁሉ፣ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፣ . . . ከአንተም ከሚወጡት ከምትወልዳቸው ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ።” (ኢሳይያስ 39:​3-7) አዎን፣ ሕዝቅያስ በሀብቱ ሊያስደምመው ያሰበው ብሔር ራሱ ከጊዜ በኋላ የኢየሩሳሌምን ግምጃ ቤት በመበዝበዝ ዜጎቿን ባሪያ ያደርጋቸዋል። ሕዝቅያስ ግምጃ ቤቱን ለባቢሎናውያን ማስጎብኘቱ የስስት ፍላጎታቸውን ይበልጥ ከማነሳሳት በቀር የፈየደው ነገር የለም!

      30. ሕዝቅያስ ጥሩ ዝንባሌ ያሳየው እንዴት ነው?

      30 ሕዝቅያስ ግምጃ ቤቱን ለባቢሎናውያን ስላስጎበኘበት አጋጣሚ ሲናገር ይመስላል 2 ዜና መዋዕል 32:​26 እንዲህ ይላል:- “ሕዝቅያስም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኩራት ሰውነቱን አዋረደ፣ የእግዚአብሔርም ቁጣ በሕዝቅያስ ዘመን አልመጣባቸውም።”

  • ንጉሡ ያሳየው እምነት ተካሰ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • b ሰናክሬም ድል ከተደረገ በኋላ የአካባቢው ብሔራት ወርቅ፣ ብርና ሌሎችንም ውድ ነገሮች በስጦታ መልክ ለሕዝቅያስ አምጥተውለታል። በ⁠2 ዜና መዋዕል 32:​22, 23, 27 ላይ “ለሕዝቅያስም እጅግ ብዙ ሀብትና ክብር” እንደሆነለትና “በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ” እንዳለ እናነባለን። ይህ ስጦታ ምናልባት ለአሦራውያን ግብር በሰጠበት ጊዜ አራቁቶት የነበረውን ግምጃ ቤቱን ለማሟላት ሳያስችለው አልቀረም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ