-
“ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት”!መጠበቂያ ግንብ—2006 | ሰኔ 15
-
-
እስራኤላውያን ገበሬዎች ከተከሉት ወይን ብዙ ምርት ለማግኘት የወይን እርሻቸውን በተገቢው ሁኔታ መንከባከብ ነበረባቸው። የኢሳይያስ መጽሐፍ ወይን የሚያመርት አንድ እስራኤላዊ ገበሬ በኮረብታ ላይ ያለውን መሬቱን እንደቆፈረና “ምርጥ የሆነውንም ወይን” ከመትከሉ በፊት በማሳው ላይ የነበረውን ትላልቅ ድንጋይ ለቅሞ እንዳስወገደ ይገልጻል። ከዚያም ምናልባት ከማሳው ላይ የለቀመውን ድንጋይ በመካብ አጥር ይሠራል። ይህ የድንጋይ ካብ የወይን እርሻው በከብቶች እንዳይረጋገጥ እንዲሁም የቀበሮ፣ የከርከሮና የሌቦች ሲሳይ እንዳይሆን ይጠብቀዋል። ቀጥሎም የወይን መጭመቂያ ጠርቦ ያዘጋጃል። በተጨማሪም ወይኑ ይበልጥ ጥበቃ ሊደረግለት በሚገባው በመከር ወቅት የሚጠለልበት አንድ አነስተኛ መጠበቂያ ማማ ይሠራ ይሆናል። ይህን ሁሉ ቅድመ ዝግጅት ካደረገ በኋላ ጥሩ የወይን ምርት ለማግኘት ይጠባበቃል።—ኢሳይያስ 5:1, 2a
-
-
“ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት”!መጠበቂያ ግንብ—2006 | ሰኔ 15
-
-
ኢሳይያስ ‘የእስራኤልን ቤት’ ውሎ አድሮ “ኮምጣጣ ፍሬ [“የዱር ወይን፣” NW]” ካፈራ የወይን ተክል ጋር አመሳስሎታል። (ኢሳይያስ 5:2, 7) ጫካ ውስጥ የሚበቅል ወይን የሚያፈራው ፍሬ መጠኑ አነስተኛ ከመሆኑም በላይ በፍሬው ውስጥ ያለው ዘር ትልቅ ነው። በመሆኑም የወይን ጠጅ ለመሥራትም ይሁን ለምግብነት የማይውለው ይህ የጫካ ወይን ከጽድቅ ይልቅ ዓመጸኝነትን ላፈራው ከሃዲ ብሔር ተስማሚ ምሳሌ ሆኖ አገልግሏል። ፍሬው እርባና ቢስ የሆነው በወይን አምራቹ ስህተት አይደለም። ይሖዋ ብሔሩ ፍሬያማ እንዲሆን የተቻለውን ሁሉ አድርጓል። በመሆኑም “ከዚህ ካደረግሁለት በላይ ለወይኔ ቦታ ምን ሊደረግለት ይገባ ነበር?” ሲል ጠይቋል።—ኢሳይያስ 5:4
-