-
“ሕዝቤን አጽናኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
12, 13. (ሀ) ተመልሶ ስለመቋቋም የተነገረው የተስፋ ቃል ሊታመን የሚችለው ለምንድን ነው? (ለ) በግዞት ለነበሩት አይሁዳውያን ምን ምሥራች ነበረ? እርግጠኞች ሊሆኑ የሚችሉትስ ለምንድን ነው?
12 ኢሳይያስ ተመልሶ ስለመቋቋም የተሰጠው የተስፋ ቃል እምነት ሊጣልበት የሚችል መሆኑን የሚያሳይ ሁለተኛ ምክንያት ይጠቅሳል። የተስፋ ቃሉን የሰጠው አምላክ ሕዝቡን በርኅራኄ የሚይዝ ኃያል አምላክ ነው። ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ይቀጥላል:- “የምስራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ [“ለጽዮን የምስራች የምትነግሪ ሆይ፣” NW ]፣ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጪ፤ የምስራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ [“ለኢየሩሳሌም የምስራች የምትነግሪ ሆይ፣” NW ] ድምፅሽን በኃይል አንሺ፤ አንሺ፣ አትፍሪ፤ ለይሁዳም ከተሞች:- እነሆ፣ አምላካችሁ! ብለሽ ንገሪ። እነሆ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ኃያል [“በኃይልም፣” የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ ] ይመጣል ክንዱም ስለ እርሱ ይገዛል፤ እነሆ፣ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደመወዙም በፊቱ ነው። መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፣ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፣ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።”—ኢሳይያስ 40:9-11
13 በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሴቶች በጦር ሜዳ ስለተገኘው ድል ወይም ሊመጣ ስላለው የተሻለ ነገር ምሥራች በመዘመር በተገኘው ውጤት የተሰማቸውን ደስታ መግለጻቸው የተለመደ ነገር ነበር። (1 ሳሙኤል 18:6, 7፤ መዝሙር 68:11 የ1980 ትርጉም ) ኢሳይያስ አይሁዳውያኑ ምርኮኞች ያላንዳች ፍርሃት ከተራራ ጫፍ ላይ በጩኸት የሚነገር ምሥራች እንደሚጠብቃቸው በትንቢታዊ መልክ መናገሩ ነበር። ይህም ይሖዋ ሕዝቡን ወደ ተወደደችው ኢየሩሳሌም መመለሱ ነው! ይሖዋ “በኃይል” ስለሚመጣ እርግጠኛ ሆነው ሊጠብቁ ይችላሉ። በመሆኑም የገባውን ቃል እንዳይፈጽም ሊያግደው የሚችል ነገር አይኖርም።
-
-
“ሕዝቤን አጽናኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
15. (ሀ) ይሖዋ ‘በኃይል’ የመጣው መቼ ነው? ‘ስለ እርሱ የሚገዛው ክንዱ’ ማን ነው? (ለ) በድፍረት ሊታወጅ የሚገባው ምሥራች የትኛው ነው?
15 የኢሳይያስ ቃላት ለዘመናችንም የሚሆን ትንቢታዊ ትርጉም ያዘሉ ናቸው። በ1914 ይሖዋ ‘በኃይል’ መጥቶ በሰማይ መንግሥቱን አቋቁሟል። ‘ስለ እርሱ የሚገዛው ክንዱ’ የተባለው ይሖዋ በሰማያዊ ዙፋን ያስቀመጠው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በ1919 ይሖዋ በምድር የነበሩትን ቅቡዓን አገልጋዮቹን ከታላቂቱ ባቢሎን ግዞት ነፃ በማውጣት ሕያውና እውነተኛ የሆነውን አምላክ አምልኮ ሙሉ በሙሉ መልሶ የማቋቋሙን ተግባር አስጀምሯል። ከዳር እስከ ዳር ይሰማ ዘንድ ይህ ምሥራች ተራራ ጫፍ ላይ ሆኖ የመጮህ ያህል በድፍረት ሊታወጅ ይገባል። እንግዲያው ይሖዋ አምላክ እውነተኛውን አምልኮ በዚህች ምድር ላይ መልሶ እንዳቋቋመ ድምፃችንን ከፍ አድርገን ለሌሎች በድፍረት እንናገር!
-