-
ከዳተኛ ለሆነው የወይን ቦታ ወዮ!የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
2 የኢሳይያስ ምሳሌ እንዲህ በማለት ይጀምራል:- “አሁን ስለ ወዳጄና ስለ ወይን ቦታው ለወዳጄ ቅኔ እቀኛለሁ። ለወዳጄ በፍሬያማው ኮረብታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው። በዙሪያው ቈፈረ፣ ድንጋዮችንም ለቅሞ አወጣ፣ ምርጥ የሆነውንም አረግ [“ቀይ ወይን፣” NW] ተከለበት፣ በመካከሉም ግንብ ሠራ፣ ደግሞም የመጥመቂያ ጉድጓድ ማሰበት፤ ወይንንም ያፈራ ዘንድ ተማመነ፣ ዳሩ ግን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ።”—ኢሳይያስ 5:1, 2፤ ከማርቆስ 12:1 ጋር አወዳድር።
-
-
ከዳተኛ ለሆነው የወይን ቦታ ወዮ!የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
4 አንድ የወይን ቦታ ፍሬ እንዲሰጥ ማድረግ ጥረት ይጠይቃል። ኢሳይያስ የወይኑ ቦታ ባለቤት ‘መሬቱን መቆፈሩንና ድንጋዮችንም ለቅሞ ማውጣቱን’ ተናግሯል። ይህ አሰልቺና አድካሚ ሥራ ነው! ‘ግንብ ለመሥራት’ የተጠቀመባቸው ትላልቆቹን ድንጋዮች ሳይሆን አይቀርም። በጥንት ዘመን እንዲህ ዓይነት ግንቦች ማሳውን ከሌቦችና ከእንስሳት ለሚጠብቁት ሰዎች እንደ ማማ ያገለግሉ ነበር።a ከዚህም ሌላ የወይን ቦታውን ለመከለል የድንጋይ ቅጥር ሠርቷል። (ኢሳይያስ 5:5) አብዛኛውን ጊዜ እንዲህ የሚደረገው በጣም አስፈላጊ የሆነው የላይኛው አፈር ተሸርሽሮ እንዳይወሰድ ለመከላከል ነበር።
5. የወይን ቦታው ጌታ ምን ነገር ለማግኘት ጠብቋል? ይሁን እንጂ ያገኘው ምንድን ነው?
5 የወይኑ ቦታ ባለቤት ለዚህ የወይን ቦታ ይህን ያህል በመድከሙ ፍሬ ያፈራል ብሎ መጠበቁ ተገቢ ነው። ይህንንም በማሰብ የመጥመቂያ ጉድጓድ ምሷል። ይሁን እንጂ ፍሬ ለመሰብሰብ የነበረው ተስፋ እውን ሆኖለታል? አልሆነለትም። እንዲያውም የወይን ቦታው ያፈራው ሆምጣጣ ፍሬ ነበር።
-
-
ከዳተኛ ለሆነው የወይን ቦታ ወዮ!የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
a አንዳንድ ምሁራን ከድንጋይ ግንብ ይልቅ በሰፊው የተለመዱት እንደ ዳስ ወይም ጎጆ ያሉት በቀላል ወጪ የሚሠሩ ጊዜያዊ ነገሮች ነበሩ የሚል እምነት አላቸው። (ኢሳይያስ 1:8) በመካከሉ የተሠራው ግንብ የወይኑ ቦታ ባለቤት ለዚህ “የወይን ቦታ” ምን ያህል የተለየ ጥረት እንዳደረገለት የሚያሳይ ነው።
-