-
“ሕዝቤን አጽናኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
14. (ሀ) ይሖዋ ሕዝቡን የሚመራበትን የርኅራኄ መንገድ ኢሳይያስ በምሳሌ ያስረዳው እንዴት ነው? (ለ) እረኞች በጎቻቸውን በርኅራኄ እንደሚይዙ የሚያሳየው የትኛው መግለጫ ነው? (ገጽ 405 ላይ የሚገኘውን ሣጥን ተመልከት።)
14 ይሁን እንጂ ይህ ኃያል አምላክ ርኅሩኅም ነው። ይሖዋ ሕዝቡን ወደ ትውልድ አገራቸው እንዴት እንደሚመራቸው ኢሳይያስ ግሩም አድርጎ ይገልጻል። ይሖዋ ጠቦቶቹን ሰብስቦ “በብብቱ” እንደሚሸከም አፍቃሪ እረኛ ነው። እዚህ ላይ “በብብቱ” የሚለው መግለጫ አጣፍቶ የሚለብሰውን ጨርቅ የሚያመለክት እንደሆነ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። አንዳንድ ጊዜ እረኞች ከሌሎቹ እኩል መሄድ የማይችሉትን አዲስ የተወለዱ ግልገሎች የሚሸከሟቸው እዚህ ውስጥ ነው። (2 ሳሙኤል 12:3) ከእረኝነት ጋር የተያያዘው እንዲህ ያለው ልብ የሚነካ መግለጫ በግዞት ለነበረው ሕዝብ የይሖዋን ፍቅራዊ አሳቢነት የሚያረጋግጥ እንደነበር ጥርጥር የለውም። በእርግጥም ደግሞ እንዲህ ያለው ኃያልና ርኅሩኅ አምላክ የገባውን ቃል እንደሚፈጽም እምነት ሊጣልበት ይችላል!
-
-
“ሕዝቤን አጽናኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
16. ይሖዋ ዛሬ ሕዝቡን የሚመራው እንዴት ነው? ይህስ ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው?
16 በኢሳይያስ 40:10, 11 ላይ የሚገኙት ቃላት በዛሬው ጊዜ ላለነው ሰዎች ተጨማሪ ጠቀሜታም አላቸው። ይሖዋ ሕዝቦቹን የሚመራበትን የርኅራኄ አያያዝ መመርመር የሚያጽናና ነው። አንድ እረኛ ከሌሎች እኩል መሄድ የማይችሉትን ጨምሮ እያንዳንዱ በግ ምን እንደሚያስፈልገው እንደሚያውቅ ሁሉ ይሖዋም እያንዳንዱ የታመነ አገልጋዩ ያለበትን የአቅም ገደብ ይገነዘባል። ከዚህም በተጨማሪ ርኅሩኁ እረኛ ይሖዋ ለክርስቲያን እረኞች ግሩም ምሳሌ ይሆናል። ሽማግሌዎች ይሖዋ ራሱ ያሳየውን ፍቅራዊ አሳቢነት በመኮረጅ መንጋውን በርኅራኄ መያዝ ይኖርባቸዋል። ይሖዋ ‘በገዛ ልጁ ደም በዋጀው’ መንጋ ውስጥ ለሚገኝ ለእያንዳንዱ አባል ምን እንደሚሰማው ዘወትር ማስታወስ ይኖርባቸዋል።—ሥራ 20:28
-
-
“ሕዝቤን አጽናኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
[በገጽ 404, 405 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]
ይሖዋ አፍቃሪ እረኛ ነው
ኢሳይያስ በጎቹን በብብቱ አቅፎ ከሚይዝ እረኛ ጋር በማወዳደር ስለ ይሖዋ ተናግሯል። (ኢሳይያስ 40:10, 11) ኢሳይያስ ይህን ምሳሌ የሰጠው በእረኞች የዕለት ተዕለት ልማድ ላይ ተመርኩዞ እንደነበር ግልጽ ነው። በመካከለኛው ምሥራቅ የሄርሞን ተራራ ላይ ያሉ እረኞችን በቅርብ የተከታተለ አንድ ታዛቢ እንዲህ ብሏል:- “እያንዳንዱ እረኛ ሁኔታቸውን ለማወቅ መንጋውን በቅርብ ይከታተላል። አዲስ የተወለደ ግልገል ሲያገኝ እናቷን ለመከተል አቅሙ ስለማይኖራት በካባው . . . ማጣፊያ ውስጥ ይይዛታል። እቅፉ ሲሞላ ደግሞ እናታቸውን መከተል እስኪችሉ ድረስ በእግራቸው እያንጠለጠለ ትከሻቸው ላይ ይሸከማቸዋል አለዚያም ቅርጫት ወይም ከረጢት ውስጥ አድርጎ በአህያ ጀርባ ላይ ይጭናቸዋል።” የምናገለግለው አምላክ ለሕዝቡ እንዲህ ያለ ርኅራኄ የተሞላበት አሳቢነት የሚያሳይ መሆኑን ማወቃችን የሚያጽናና አይደለምን?
-