-
“ሕዝቤን አጽናኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
17, 18. (ሀ) አይሁዳውያኑ ግዞተኞች ተመልሰው እንደሚቋቋሙ በተሰጠው የተስፋ ቃል ላይ ትምክህት ሊኖራቸው የሚችለው ለምንድን ነው? (ለ) ኢሳይያስ ያነሳቸው የሚያስፈሩ ጥያቄዎች የትኞቹ ናቸው?
17 የአምላክ ኃይልና ጥበብ አቻ የማይገኝለት በመሆኑ ግዞተኞቹ አይሁዳውያን ተመልሰው እንደሚቋቋሙ በተሰጠው የተስፋ ቃል ሊተማመኑ ይችላሉ። ኢሳይያስ እንዲህ ይላል:- “ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፣ ሰማይንም በስንዝር የለካ፣ የምድርንም አፈር በመስፈርያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው? የእግዚአብሔርን መንፈስ ያዘዘ፣ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያስተማረው ማን ነው? ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍርድንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው?”—ኢሳይያስ 40:12-14
18 እነዚህ በግዞት ላይ የነበሩት አይሁዳውያን ሊያሰላስሉባቸው የሚገቡ አክብሮታዊ ፍርሃት የሚያሳድሩ ጥያቄዎች ናቸው። ሥጋ ለባሽ የሆነው ሰው የአንድን ትልቅ ባሕር ሞገድ ሊያስቆም ይችላልን? እንዴት አድርጎ! ይሁንና በይሖዋ ፊት ምድርን የሸፈኗት ባሕሮች በመዳፉ ላይ እንዳለች አንድ ጠብታ ናቸው።b ደካማ የሆኑ ሰዎች ከዋክብት የሞሉበትን ሰፊ ሰማይ መለካት ወይም የምድርን ተራሮችና ኮረብቶች መመዘን ይችላሉን? በፍጹም። ይሖዋ ግን ሰው አንድን ነገር በስንዝር ማለትም ከአውራ ጣቱ እስከ ትንሿ ጣቱ ጫፍ ድረስ ባለው ርቀት መለካት እንደሚችል ሁሉ በቀላሉ ሊለካቸው ይችላል። አምላክ ተራሮችንና ኮረብቶችን በሚዛን ሊለካቸው የሚችል ያህል ነው። ከሰዎች መካከል እጅግ ጠቢብ የሚባሉት እንኳ ቢሆኑ አሁን ስላለውም ሁኔታ ይሁን ወደፊት ስለሚመጣው ነገር እንዲህ አድርግ ብለው አምላክን ሊያማክሩት ይችላሉን? በፍጹም አይችሉም!
-
-
“ሕዝቤን አጽናኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
b “አጠቃላዩ የውቂያኖሶች መጠነቁስ (mass) 1.35 ኳንቲሊየን (1.35 x 1018) ሜትሪክ ቶን ወይም ከጠቅላላው የምድር መጠነቁስ 1/4400 እንደሚሆን” ይገመታል።—ኢንካርታ 97 ኢንሳይክሎፔዲያ
-