-
“ሕዝቤን አጽናኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
19, 20. የይሖዋን ታላቅነት ጎላ አድርጎ ለመግለጽ ኢሳይያስ ምን ስዕላዊ መግለጫ ተጠቅሟል?
19 በምድር ስላሉት ኃያላን ብሔራትስ ምን ለማለት ይቻላል? አምላክ የተስፋ ቃሉን እንዳይፈጽም ሊገቱት ይችሉ ይሆን? ኢሳይያስ ብሔራትን እንደሚከተለው ብሎ በመግለጽ መልስ ይሰጣል:- “እነሆ፣ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፣ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ እነሆ፣ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል። ሊባኖስ ለማንደጃ እንስሶችዋም ለሚቃጠል መሥዋዕት አይበቁም። አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፤ ከምናምን እንደሚያንሱ፣ እንደ ከንቱ ነገርም ይቈጥራቸዋል።”—ኢሳይያስ 40:15-17
20 ብሔራት በጠቅላላ በይሖዋ ፊት በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው። ምንም ለውጥ እንደማያመጣ በሚዛን ላይ እንዳለ ደቃቅ ትቢያ ከመሆን አያልፉም።c አንድ ሰው ትልቅ መሠዊያ ገንብቶ የሊባኖስን ተራሮች የሸፈኑትን ዛፎች ሁሉ ማገዶ ቢያደርግና በተራራው ላይ የሚዘዋወሩትን እንስሳት ሁሉ መሥዋዕት አድርጎ ቢያቀርባቸው እንኳ ለይሖዋ የሚበቃ አይሆንም። ኢሳይያስ እስካሁን የተጠቀመባቸው መግለጫዎች ሁሉ በቂ ስላልሆኑ ሌላ የበለጠ ጠንከር ያለ መግለጫ በመጠቀም ብሔራት ሁሉ በይሖዋ ዓይን “ከምንም ያነሱ” ናቸው ብሏል።—ኢሳይያስ 40:17፣ ኒው ሪቫይዝድ ስታንዳርድ ቨርሽን
-
-
“ሕዝቤን አጽናኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
c ዚ ኤክሲፖዚተርስ ባይብል ኮሜንታሪ እንዲህ ይላል:- “በምሥራቃውያን የገበያ ቦታ በሚካሄደው ንግድ ፈሳሽ ነገሮች በሚለኩበት ገንቦ ውስጥ ያለችውን ትንሽ የውኃ ጠብታ ወይም ደግሞ ሥጋ አሊያም ፍራፍሬ ሲመዘን በሚዛን ላይ የሚኖረውን ትቢያ ከግምት ውስጥ የሚያስገባ የለም።”
-