የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ሕዝቤን አጽናኑ”
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • [በገጽ 412 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]

      የምድር ቅርጽ ምን ዓይነት ነው?

      በጥንት ዘመን አብዛኛው ሰው የሚያስበው ምድር ጠፍጣፋ እንደሆነች ነበር። በስድስተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ መጀመሪያ ላይ ግሪካዊው ፈላስፋ ፓይታጎረስ ምድር ሉል መሆን አለባት የሚል ጽንሰ ሐሳብ አፈለቀ። ያም ሆኖ ግን ፓይታጎረስ ይህንን ጽንሰ ሐሳብ ከማፍለቁ ሁለት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስ አስገራሚ በሆነ ግልጽነትና እርግጠኝነት “እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀመጣል” ሲል ተናግሯል። (ኢሳይያስ 40:​22፣ በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።) እዚህ ላይ “ክበብ” ተብሎ የተተረጎመው ኩግ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል “ሉል” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። የሚያስገርመው ደግሞ ከየትኛውም አቅጣጫ ክብ ሆኖ የሚታየው የሉል ቅርጽ ያለው ነገር ብቻ ነው።e በዚህ መንገድ ነቢዩ ኢሳይያስ በዘመኑ ከነበረ ግምታዊ ሐሳብ የጸዳና ከትክክለኛ ሳይንስ ጋር የሚጣጣም ሐሳብ መዝግቧል።

      [የግርጌ ማስታወሻ]

      e ምድር ጥፍጥፍ ሉልመሳይ (oblate spheroid) ነች ለማለት ይቻላል። በዋልታዎቿ አካባቢ በተወሰነ መጠን ጠፍጣፋ ቅርጽ አላት።

  • “ሕዝቤን አጽናኑ”
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 21, 22. (ሀ) ይሖዋ አቻ የሌለው መሆኑን ኢሳይያስ ጎላ አድርጎ የገለጸው እንዴት ነው? (ለ) ሕያው የሆነው የኢሳይያስ መግለጫ ወደ ምን መደምደሚያ ያደርሰናል? (ሐ) ነቢዩ ኢሳይያስ ሳይንሳዊ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ምን ነገር ተናግሯል? (ገጽ 412 ላይ የሚገኘውን ሣጥን ተመልከት።)

      21 ኢሳይያስ፣ ይሖዋ አቻ የማይገኝለት አምላክ መሆኑን ይበልጥ ጠበቅ አድርጎ ለመግለጽ ሲል ከወርቅ፣ ከብር ወይም ከእንጨት አማልክት የሚሠሩትን ሰዎች የሞኝነት ድርጊት ማጋለጡን ይቀጥላል። እንዲህ ያለ ማንኛውም ጣዖት ‘በምድር ክበብ ላይ የሚቀመጠውን ’ እና ነዋሪዎቿን የሚመለከተውን አምላክ ይወክላል ብሎ ማሰብ ምንኛ ሞኝነት ይሆናል!​—⁠ኢሳይያስ 40:​18-24ን አንብብ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ