-
ከዳተኛ ለሆነው የወይን ቦታ ወዮ!የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
6, 7. (ሀ) የወይን ቦታው ጌታ ማን ነው? የወይን ቦታውስ? (ለ) ጌታው ምን ፍርድ እንዲሰጠው ጠይቋል?
6 የወይኑ ቦታ ባለቤት ማን ነው? የወይኑ ቦታስ ምንድን ነው? የወይኑ ቦታ ባለቤት ራሱ የሚከተለውን በማለት ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሱን ይሰጣል:- “አሁንም እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎችም ሆይ፣ በእኔና በወይኑ ቦታዬ መካከል እስኪ ፍረዱ። ለወይኔ ያላደረግሁለት፣ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ስተማመን ስለ ምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ? አሁንም በወይኔ ላይ የማደርገውን እነግራችኋለሁ፤ አጥሩን እነቅላለሁ፣ ለማሰማርያም ይሆናል፤ ቅጥሩንም አፈርሳለሁ፣ ለመራገጫም ይሆናል።”—ኢሳይያስ 5:3-5
-
-
ከዳተኛ ለሆነው የወይን ቦታ ወዮ!የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
9. ይሖዋ ብሔሩን ከፍ ያለ ዋጋ እንዳለው የወይን ቦታ አድርጎ የያዘው እንዴት ነው?
9 ይሖዋ ሕዝቡን በከነዓን ምድር ‘በመትከል’ ሕጉንና መመሪያውን ሰጥቷቸዋል። ይህም በሌሎች ብሔራት እንዳይበከሉ እንደ አጥር ሆኖ አገልግሏል። (ዘጸአት 19:5, 6፤ መዝሙር 147:19, 20፤ ኤፌሶን 2:14) ከዚህም በላይ ይሖዋ የሚያስተምሯቸውንና መመሪያ የሚሰጡአቸውን መሳፍንት፣ ካህናትና ነቢያት ሰጥቷቸዋል። (2 ነገሥት 17:13፤ ሚልክያስ 2:7፤ ሥራ 13:20) እስራኤላውያን ወታደራዊ ዛቻ በደረሰባቸው ጊዜ የሚታደጓቸውን ሰዎች አስነስቶላቸዋል። (ዕብራውያን 11:32, 33) ይሖዋ “ለወይኔ ያላደረግሁለት፣ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው?” ብሎ መጠየቁ ያለ ምክንያት አልነበረም።
-